ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ (Telat Aynu Eyaye) - ታጋይ ፡ ወልደማርያም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ታጋይ ፡ ወልደማርያም
(Tagay Woldemariam)

Tagay Woldemariam 2.jpg


(2)

ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ
(Telat Aynu Eyaye)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታጋይ ፡ ወልደማርያም ፡ አልበሞች
(Albums by Tagay Woldemariam)

ለአንተ ፡ ያልተቻለ ፡ ለአንተ ፡ ያቃተህ
ምንም ፡ ነገር ፡ የለም ፡ ለአንተ ፡ የሚሳንህ
ጠላት ፡ ምን ፡ ቢፎክር ፡ ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ ነው
ድንገት ፡ ስትነሳ ፡ አድራሻው ፡ ሲኦል ፡ ነው

አዝ፦ በከፍታ ፡ ላይ ፡ ታቆማለህ
ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ
እራስን ፡ በዘይት ፡ ትቀባለህ
ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ
የተዘጋን ፡ በር ፡ ትከፍታለህ
ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ
አንደበትን ፡ በሳቅ ፡ ትሞላለህ
ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ

ቃል ፡ ካፍህ ፡ ከወጣ ፡ አንተ ፡ ከተናገርህ
የማይሆን ፡ ምን ፡ አለ ፡ ትዕዛዝ ፡ ካወጣህ
የጨለመ ፡ ቢመስል ፡ ቀናት ፡ ቢቆጠሩም
ዘመኑን ፡ ጠብቆ ፡ መንጋቱ ፡ አይቀርም

አዝ፦ በከፍታ ፡ ላይ ፡ ታቆማለህ
ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ
እራስን ፡ በዘይት ፡ ትቀባለህ
ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ
የተዘጋን ፡ በር ፡ ትከፍታለህ
ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ
አንደበትን ፡ በሳቅ ፡ ትሞላለህ
ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ

አዋጅ ፡ ታውጆበት ፡ ሞቱን ፡ ሲጠባበቅ
ከሳሹ ፡ ሲፎክር ፡ ነፍሱ ፡ ስትጨነቅ
ድንገት ፡ ሳይታሰብ ፡ ታሪክ ፡ ተገልብጦ
ዛሬም ፡ ይዘምራል ፡ ከፍታውን ፡ ረግጦ

አዝ፦ በከፍታ ፡ ላይ ፡ ታቆማለህ
ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ
እራስን ፡ በዘይት ፡ ትቀባለህ
ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ
የተዘጋን ፡ በር ፡ ትከፍታለህ
ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ
አንደበትን ፡ በሳቅ ፡ ትሞላለህ
ጠላት ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ

ተለወጠ ፡ ነገር ፡ ተለወጠ
ተለወጠ ፡ ታሪክ ፡ ተለወጠ
የጠላት ፡ ከፍታው ፡ ተረገጠ
ተለወጠ ፡ ነገር ፡ ተለወጠ
ተለወጠ ፡ ታሪክ ፡ ተለወጠ
የወንድሞች ፡ ከሳሽ ፡ ተረገጠ
ጠላት ፡ ተረገጠ ፡ ሰይጣን ፡ ተረገጠ
ሟርተኛው ፡ ተረገጠ ፡ ደጋሚው ፡ ተረገጠ