From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ብዙ ፡ ዘመን ፡ የተሸክምከኝ
በሃሩሩ ፡ ጥላ ፡ የሆንክልኝ
በዘላለም ፡ ፍቅርህ ፡ የወደድከኝ
ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ
ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ
ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ
ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ (፪x)
ውለታህን ፡ ከቶ ፡ አልረሳውም
በቃላት ፡ ልገልጸው ፡ እኔ ፡ አልችልም
ለአንተ ፡ በመሰጠት ፡ ከነፍሴ
ላክብርህ ፡ ላንግስህ ፡ ኢየሱሴ
ለአንተ ፡ በመሰጠት ፡ ከነፍሴ
ላክብርህ ፡ ላንግስህ ፡ ኢየሱሴ (፪x)
ወደኸኛል ፡ አና ፡ አዳንከኝ
በምህረትህ ፡ ዳግም ፡ አሰብከኝ
ልዩ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ፍቅርህ
አስገረመኝ ፡ እኔን ፡ መወደድህ) (፪x)
አዝ፦ ብዙ ፡ ዘመን ፡ የተሸክምከኝ
በሃሩሩ ፡ ጥላ ፡ የሆንክልኝ
በዘላለም ፡ ፍቅርህ ፡ የወደድከኝ
ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ (፬x)
ውለታህን ፡ ከቶ ፡ አልረሳውም
በቃላት ፡ ልገልጸው ፡ እኔ ፡ አልችልም
ለአንተ ፡ በመሰጠት ፡ ከነፍሴ
ላክብርህ ፡ ላንግስህ ፡ ኢየሱሴ) (፪x)
ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ ፍቅርህ ፡ ደንቆኛል
እጄን ፡ በአፌ ፡ አስጭኖኛል
ለአንተ ፡ ከመዘመር ፡ ለዘለዓለም
ላፍታ ፡ ወደኋላ ፡ አልልም (፪x)
አምላኬን ፡ ጠርቸው ፡ አላፈርኩም
በእርሱ ፡ ተማምኜም ፡ አልከሰርኩም
ስጠራው ፡ በድንገት ፡ ደርሶልኛል
በከፍታዎች ፡ ላይ ፡ አቁሞኛል
ስጠራው ፡ በድንገት ፡ ደርሶልኛል
በከፍታዎች ፡ ላይ ፡ አቁሞኛል (፪x)
ውለታህን ፡ ከቶ ፡ አልረሳውም
በቃላት ፡ ልገልጸው ፡ እኔ ፡ አልችልም
ለአንተ ፡ በመሰጠት ፡ ከነፍሴ
ላክብርህ ፡ ላንግስህ ፡ ኢየሱሴ) (፪x)
ወድቄ ፡ አልቀረሁም ፡ ተነሳሁኝ
በአምላኬ ፡ ዳግመኛ ፡ ታሰብኩኝ
ዛሬ ፡ በሰገነት ፡ ላይ ፡ ቆሜ
ሰዋለሁ ፡ ምሥጋና ፡ ደጋግሜ (፪x)
ወድቄ ፡ አልቀረሁም ፡ ተነሳሁኝ
በአምላኬ ፡ ዳግመኛ ፡ ታሰብኩኝ
ዛሬ ፡ በሰገነት/በከፍታዎች ፡ ላይ ፡ ቆሜ
እሰዋለሁ ፡ ምሥጋና ፡ ደጋግሜ (፪x)
አዝ፦ ብዙ ፡ ዘመን ፡ የተሸክምከኝ
በሃሩሩ ፡ ጥላ ፡ የሆንክልኝ
በዘላለም ፡ ፍቅርህ ፡ የወደድከኝ
ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ
ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ
ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ
ኢየሱሴ ፡ ተባረክልኝ (፪x)
|