From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ከስትንፋሴ ይልቅ ታስፈልገኛለህ
ከምስበው አየር ለኔ ትበልጣለህ
እተነፍሳለሁ አየሬ ነህ እተነፍሳለሁ
እተነፍሳለሁ ኢየሱሴን እተነፍሳለሁ
እተነፍሳለሁ ኢየሱሴን እተነፍሳለሁ
ህይወት ማለት ካንተ ጋራ ያለኝ ህብረት ነው በቃ
ምን ዋጋ አለው ሁሉ ሞልቶት በህይወቱ ሰው አንተን ካጣ
አንተን ይዤ ተራ መሆን እኔ አልችልም
ውስጤ ያለው ያንተ መንፈስ ቀልድ አይደለም
እንደጥንቱ ኢየሱስ ኢየሱስ ያሰኘኛል
ፍለጋዬ ከትናንቱ እጅግ ብሷል
እፈልግሃለሁ ሁልጊዜ ሁልጊዜ
እፈልግሃለሁ ዋናዬ ነህ ኢየሱሴ
እፈልግሃለሁ ሁልጊዜ ሁልጊዜ
እፈልግሃለሁ ዋናዬ ነህ ኢየሱሴ
መኖር ማለት ካንተ ጋራ በመንፈስህ ውስጥ ማደር ነው
አንተ ደሞ ከሌለኸኝ በቃ እኔ የለሁም ነው
ህይወት ማለት በህልውና በምንፈስህ ውስጥ ማደር ነው
ጌታ ኢየሱስ ከሌለማ በቃ እኛ የለንም ነው
ኢየሱስ ዋናዬ ነው ኢየሱስ ዋናዬ×4
ልተካው ማልችለው በምንም እኔ
እፈልግሃለሁ ሁልጊዜ ሁልጊዜ
እፈልግሃለሁ ዋናዬ ነህ ኢየሱሴ
እፈልግሃለሁ ሁልጊዜ ሁልጊዜ
እፈልግሃለሁ ዋናዬ ነህ ኢየሱሴ
መኖር ማለት ካንተ ጋራ በመገኘትህ ማደር ነው
አንተ ደሞ በሌለህበት በቃ እኛ የለንም ነው
ህይወት ማለት በህልውና በምንፈስህ ውስጥ ማደር ነው
ጌታ ኢየሱስ ከሌለማ በቃ እኛ የለንም ነው
ኢየሱስ ዋናዬ ነው ኢየሱስ ዋናዬ×4
ልተካው ማልችለው በምንም እኔ
እፈልግሃለሁ ሁልጊዜ ሁልጊዜ
እፈልግሃለሁ ዋናዬ ነህ ኢየሱሴ
እፈልግሃለሁ ሁልጊዜ ሁልጊዜ
እፈልግሃለሁ ዋናዬ ነህ ኢየሱሴ
መኖር ማለት ካንተ ጋራ በመንፈስህ ውስጥ ማደር ነው
አንተ ደሞ ከሌለኸኝ በቃ እኔ የለሁም ነው
ኢየሱስ ዋናዬ ነው ኢየሱስ ዋናዬ×4
ልተካው ማልችለው በምንም እኔ
|