From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዲስ ፡ ልዩ ፡ ነገድ ፡ ተገኝቷል
ከአስራ ፡ ሁለቱ ፡ አይደል ፡ ከእስራኤል (፪x)
እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ዐይነቱ ፡ የነገዱ
ሃያል ፡ ገናና ፡ ነው ፡ ንጉሡ
የጸና ፡ መንግሥቱ (፪x)
ዜግነት ፡ ቢሉ ፡ ሰማያዊ
አለቃው ፡ የሰማይ ፡ የምድር ፡ ፈጣሪ
አለ ፡ የሚኖር ፡ ዘለዓለማዊ
አዝ:- (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ ወደዚህ ፡ መንግሥት ፡ ሲጋብዘኝ
(አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ አዲስ ፡ ዜግነት ፡ እስኪሰጠኝ
(አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ ወደዚህ ፡ ግዛት ፡ ሲጋብዘኝ
(አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ አዲስ ፡ ማንነት ፡ እንዲሰጠኝ
እኔም ፡ ግዛቱ ፡ ለመግባት ፡ አሰብኩኝ
ህገመንግሥቱን ፡ አነበብኩኝ ፡ የተጻፈውን ፡ አንበብኩኝ
መግቢያው ፡ መወለድ ፡ ነው ፡ ዳግም
የመስቀሉን ፡ ሃይል ፡ አምኖ ፡ መቀበል (፪x)
መቀበል ፡ ማመን ፡ በልጁ
በመንፈስ ፡ ዳግም ፡ መወለዱ
ሌላም ፡ አይደለም ፡ ይሄው ፡ ነው ፡ መንገዱ
አዝ:- (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ በማመን ፡ ብቻ ፡ ሲቀበለኝ
(አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ ልጁን ፡ ስቀበል ፡ ተ???በለኝ
(አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ አባቴ ፡ ሆኖ ፡ ልጄ ፡ ሲለኝ
(አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ ለዘለዓለም ፡ ኑሪ ፡ ሲለኝ
ጽዮናዊ ፡ ነኝ ፡ በዜግነት ፡ አሁንማ
ተረሳስተናል ፡ ከዓለም ፡ ጋራ ፡ ተካክደናል ፡ ከዓለም ፡ ጋራ
ሰማያዊ ፡ ነው ፡ ሚናፍቀኝ ፡ የማስበው
የምድርን ፡ ንቄ ፡ ትቼዋለሁ ፡ ጽዮንን ፡ ተመኘሁ (፪x)
ጨለማው ፡ ጠፍቶ ፡ በርቻለሁ
ሰማያዊ ፡ ነው ፡ የምናገረው
ስፍራ ፡ ቀይሬ ፡ በቀኙ ፡ ሆኛለሁ
አዝ:- (አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ በቀኙ ፡ በኩል ፡ አስቀመጠኝ
(አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ ቋንቋዬን ፡ ሁሉ ፡ ቀየረልኝ
(አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ አዲስ ፡ ማንነት ፡ አገኘሁኝ
(አስገረመኝ ፡ አስደነቀኝ) ፡ ወደ ፡ መንግሥቱ ፡ ገላገለኝ
|