From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እንዴት ፡ አልፈዋለሁ ፡ ያልኩትን ፡ ያንን ፡ ቀን
ክንድህ ፡ አሻገረኝ ፡ አለፍኩት ፡ ያንን ፡ ቀን
ዛሬስ ፡ ተረዳሁኝ ፡ ቆምኩኝ ፡ እንደገና
ቀና ፡ አልኩኝ ፡ ከአንገቴ ፡ ታለፈ ፡ ያ ፡ ዘመን
ታለፈ ፡ ያ ፡ ዘመን (፬x)
(በኢየሱስ ፡ የማይታለፍ ፡ ምን ፡ አለ)
ታለፈ ፡ ያ ፡ ዘመን (፬x)
ምንም ፡ ሳልናገር ፡ ቃል ፡ ሳይወጣ ፡ ከአፌ
ሁሉን ፡ መለሰና ፡ ሆነልኝ ፡ ድጋፌ
ያ ፡ ሁሉ ፡ ጥያቄ ፡ ኧረ ፡ ወዴት ፡ ገባ
ማንስ ፡ አበሰልኝ ፡ የዓይኖቼን ፡ እንባ
እንደ ፡ እናትም ፡ ሆነ ፡ ከእናትም ፡ በላይ
ብዙ ፡ አድርጐልኛል ፡ ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ
እንደ ፡ አባትም ፡ ሆነ ፡ ከአባትም ፡ በላይ
ብዙ ፡ አድርጐልኛል ፡ ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ (፪x)
መግለጥ ፡ አቅቶኝ ፡ ፍቅርህን ፡ በቋንቋ
ብዘምር ፡ ብዘምር ፡ ብሎኛል ፡ አሎወጣ
እስኪ ፡ ልሞክር ፡ ለመግለጽ ፡ ስለ ፡ አንተ
ደግሜ ፡ ልበልህ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ፍቅር ፡ ነህ
አንተ ፡ እኮ ፡ ፍቅር ፡ ነህ (፮x)
አንተ ፡ እኮ ፡ ደግ ፡ ነህ (፮x)
አንተ ፡ እኮ ፡ ሩሩህ ፡ ነህ (፮x)
እንዴት ፡ አልፈዋለሁ ፡ ያልኩትን ፡ ያንን ፡ ቀን
ክንድህ ፡ አሻገረኝ ፡ አለፍኩት ፡ ያንን ፡ ቀን
ዛሬስ ፡ ተረዳሁኝ ፡ ቆምኩኝ ፡ እንደገና
ቀና ፡ አልኩኝ ፡ ከአንገቴ ፡ ታለፈ ፡ ያ ፡ ዘመን
ታለፈ ፡ ያ ፡ ዘመን (፫x)
ታለፈ ፡ ያ ፡ ዘመን ፡ (በኢየሱስ ፡ የማይታለፍ ፡ ምን ፡ አለ)
ታለፈ ፡ ያ ፡ ዘመን (፬x)
|