ምን ፡ ይለኛል (Men Yelegnal) - መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ
(Mesfin Gutu)

Mesfin Gutu Esp.png

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ሰላም ፡ ነው
(Selam New)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(6)

ጸሐፊ (Writer): መስፍን ፡ ጉቱ
(Mesfin Gutu
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Mesfin Gutu)

ምን ይለኛል/2 የሆነልኝ ነገር ሚስጥሩ ያልገባው አዎ
ምን ይለኛል/2 እኔስ እንደዳዊት እርቃኔን ባመልከው አዎ
ምን ይለኛል/2 ብዬስ አምልኮዬን ፈፅሞ አልቀንስም አዎ
ምን ይለኛል/2 የሆነልኝ ነገስ ዝምም አያሰኝም አዎ

ያለውን ይበል እንጂ ያሻውን አንደልቡ
ያልገባው ያልተረዳው ቢተቸኝ እንዳሰቡ
ከትቢያ ላይ ላነሳኝ ለክብሩ ዘምራለው
ከውርደቴ ላሰበኝ ለስሙ እቀኛለው

የምስኪን ወዳጅ ለደሃደጉ
አባት ለሌለው ክብሩ ማዕረጉ
ያየ ይመስክር የማይረሳ ሰው
ያለፍኩበትን እኔስ አልረሳው

ውለታውን እስኪ ላነሳሳው እንዴት ልርሳው/4

እንዴት እንደረዳኝ እኔ ነኝ የማውቀው
ከየት እንዳነሳኝ እኔ ነኝ የማውቀው

ውለታውን እስኪ ላነሳሳው እንዴት ልርሳው/2

ፍቅሩን ምህረቱን ቀምሼዋለው
እንደ እየሱሴማ የት አገኛለው
እድሜ ዘመኔን ለእርሱ ብዘምር
አልጨርሰው ሁሉን ብናገር

ውለታውን እስኪ ላነሳሳው እንዴት ልርሳው/4

ምን ይለኛል/2 የሆነልኝ ነገር ሚስጥሩ ያልገባው አዎ
ምን ይለኛል/2 እኔስ እንደዳዊት እርቃኔን ባመልከው አዎ
ምን ይለኛል/2 ብዬስ አምልኮዬን ፈፅሞ አልቀንስም አዎ
ምን ይለኛል/2 የሆነልኝ ነገስ ዝምም አያሰኝም አዎ

ያለውን ይበል እንጂ ያሻውን አንደልቡ
ያልገባው ያልተረዳው ቢተቸኝ እንዳሰቡ
ከትቢያ ላይ ላነሳኝ ለክብሩ ዘምራለው
ከውርደቴ ላሰበኝ ለስሙ እቀኛለው