From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ የታመንኩትን ፡ አውቀዋለሁ
በወጀብ ፡ ውስጥ ፡ መንገድ ፡ አለው
የታመንኩትን ፡ አውቀዋለሁ
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ መንገድ ፡ አለው
መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታዬ ፡ መንገድ ፡ አለው
መንገድ ፡ አለው ፡ ኢየሱሴ ፡ መንገድ ፡ አለው (፪x)
ሰባት ፡ አጥፍ ፡ እሳት ፡መንገድ ፡ አለው ፡ ጠላቶ ፡ ቢያነድም
ላቆመው ፡ ምስል ፡ ከቶ ፡ እኔ ፡ አልሰግድም
በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ መንገድ ፡ አለውና
እኔ ፡ እንደው ፡ አልፈራ ፡ እምላኬ ፡ አለና [1]
አዝ፦ የታመንኩትን ፡ አውቀዋለሁ
በወጀብ ፡ ውስጥ ፡ መንገድ ፡ አለው
የታመንኩትን ፡ አውቀዋለሁ
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ መንገድ ፡ አለው
መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታዬ ፡ መንገድ ፡ አለው
መንገድ ፡ አለው ፡ ኢየሱሴ ፡ መንገድ ፡ አለው (፪x)
በዳንኤል ፡ ፀሎት ፡ በእጅጉ ፡ የተከፋ
ከአንበሳ ፡ ጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ ጣለው ፡ እንዲጠፋ
መላዕክቶችን ፡ ልኮ ፡ የአንበሳን ፡ አፍ ፡ ዘጋ [2]
ዛሬም ፡ ብርቱ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ለህዝቡ ፡ ሊዋጋ
አዝ፦ የታመንኩትን ፡ አውቀዋለሁ
በወጀብ ፡ ውስጥ ፡ መንገድ ፡ አለው
የታመንኩትን ፡ አውቀዋለሁ
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ መንገድ ፡ አለው
መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታዬ ፡ መንገድ ፡ አለው
መንገድ ፡ አለው ፡ ኢየሱሴ ፡ መንገድ ፡ አለው (፪x)
ሃማ ፡ ቁጣው ፡ ቢነድ ፡ ቢዝትም ፡ አብዝቶ
የንጉሥ ፡ ባለሟል ፡ በመሆኑ ፡ ኮርቶ
ህዝቡን ፡ ለጣላቶች ፡ አሳልፎ ፡ የማይሰጥ
በጊዜው ፡ ደረሰ ፡ ምክሩን ፡ ሊገለብጥ [3]
አዝ፦ የታመንኩትን ፡ አውቀዋለሁ
በወጀብ ፡ ውስጥ ፡ መንገድ ፡ አለው
የታመንኩትን ፡ አውቀዋለሁ
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ መንገድ ፡ አለው
መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታዬ ፡ መንገድ ፡ አለው
መንገድ ፡ አለው ፡ ኢየሱሴ ፡ መንገድ ፡ አለው (፪x)
ጠላቴ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አጅግ ፡ በርትቶብኝ
አምላክህ ፡ የት ፡ አለ ፡ እስኪ ፡ ያድንህ ፡ ሲለኝ
ኃይለኛው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፈጥኖ ፡ ደረሰና
ሀሳቡን ፡ በተነው ፡ አደረገው ፡ መና
አዝ፦ የታመንኩትን ፡ አውቀዋለሁ
በወጀብ ፡ ውስጥ ፡ መንገድ ፡ አለው
የታመንኩትን ፡ አውቀዋለሁ
በእሳት ፡ ውስጥ ፡ መንገድ ፡ አለው
መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታዬ ፡ መንገድ ፡ አለው
መንገድ ፡ አለው ፡ ኢየሱሴ ፡ መንገድ ፡ አለው (፪x)
|
- ↑ ዳንኤል ፫ (Daniel 3)
- ↑ ዳንኤል ፮ (Daniel 6)
- ↑ አስቴር ፡ ፮ ፡ ፩ - ፯ ፡ ፲ (Esther 6:1 - 7:10)