ዝናህ ፡ የገነነው (Zenah Yegenenew) - መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
መሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ
(Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold 2.jpg


(2)

ዝናህ ፡ የገነነው
(Zenah Yegenenew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የመሠረት ፡ ፅጌና ፡ እንዳልካቸው ፡ ኪዳነወልድ ፡ አልበሞች
(Albums by Meseret Tsegie and Endalkachew Kidanewold)

በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ልጽና ፡ በመንፈስህ ፡ እንዳልረታ
አርቄ ፡ እያየሁ ፡ የጽድቅ ፡ አክሊልን
በተስፋ ፡ እንድጓዝ ፡ እርዳኝ ፡ ልጅህን
የርስቴ ፡ መያዣ ፡ መንፈስህን
ያጽናናኝ ፡ ሁልጊዜ ፡ እንዳልረሳህ
(፪x)

የማትሰለቸኝ ፡ የማትረሳኝ
ረዳት ፡ ለጉዞዬ ፡ ለነፍሴ ፡ አጽናኝ
ዓይኔን ፡ እንዳላነሳው ፡ ከመስቀልህ
ሃሳቤን ፡ ጠቅልለው ፡ ወደ ፡ ሞትህ (፫x)

ዝናህ ፡ የገነነው ፡ በዓለም ፡ ላይ
መቼ ፡ ትመጣለህ ፡ ፊትህን ፡ እንዳይ
በጣም ፡ ጓጉቻለሁ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ኢየሱሴ ፡ እንዳይህ ፡ ማራናታ
(፬x)