ነፍሴ ፡ ወደሱ ፡ አደላ (Nefsie Wedesu Adela) - ምህረት ፡ ኢተፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ምህረት ፡ ኢተፋ
(Meheret Etefa)


(5)

ነፍሴ ፡ ወደሱ ፡ አደላ
(Nefsie Wedesu Adela)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2013)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:52
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የምህረት ፡ ኢተፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Meheret Etefa)

አዝነፍሴ ፡ ወደ ፡ እሱ ፡ አደላ (፭x)
ነፍሴ ፡ ለእርሱ ፡ ቅርብ ፡ ነው (፭x)
እስቲ ፡ አናምጧቸው ፡ እስቲ ፡ አንያቸው
ሌሎች ፡ ሌሎቹን ፡ እንመዝናቸው
አማራጭና ፡ ምትክ ፡ የሌለው
ለእኔ ፡ ጌታዬ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
የማያዳክም ፡ አራት ፡ ነጥብ ፡ ነው

ቆይ ፡ ቆቆይ ፡ ቆቆይ ፡ ቆቆይ ፡ ቆይ ፡ እስቲ ፡ አሃ ፡ ቆይ
ቆይ ፡ ቆቆይ ፡ ቆቆይ ፡ ቆቆይ ፡ ቆይ ፡ እስቲ ፡ አሃ
ማነውስ ፡ ለጠላቱ ፡ ሕይወቱን ፡ የሚሰጠው
ስለ ፡ ፍቅር ፡ ብሎ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ የሚሞተው

ነፍሴ ፡ ያደላው ፡ ለእርሱ ፡ ነው (፪x)
ልቤ ፡ ያደላው ፡ ለእርሱ ፡ ነው (፫x)

አላይም ፡ ሌላውን ፡ አላይም ፡ ሌላውን ፡ አላይም (፬x)
ሁሌም ፡ የምትሸከመኝ ፡ የማትዝል ፡ የማትደክምብኝ
እውነተኛ ፡ ወዳጄ ፡ ማነው ፡ እንዳንተ ፡ ሚሆነኝ
አሃሃሃ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ በላይ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ ክበርልኝ/ንገስልኝ (፪x)

አላይም ፡ ሌላውን ፡ አላይም ፡ ሌላውን ፡ አላይም (፬x)
በመመዘኛ ፡ ሚዛን ፡ ላይ ፡ ሁሉንም ፡ ሳያቸው
የእኔ ፡ አምላክ ፡ ብቻ ፡ ከበደ ፡ ሚዛኑን ፡ ደፋ ፡ አደረገው
አሃሃሃ ፡ የሁሉም ፡ የበላይ ፡ የሁሉም ፡ የበላይ ፡ እርሱ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ እሱ ፡ አደላ (፭x)
ነፍሴ ፡ ለእርሱ ፡ ቅርብ ፡ ነው (፭x)
እስቲ ፡ አናምጧቸው ፡ እስቲ ፡ አንያቸው
ሌሎች ፡ ሌሎቹን ፡ እንመዝናቸው
አማራጭና ፡ ምትክ ፡ የሌለው
ለእኔ ፡ ጌታዬ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
የማያዳክም ፡ አራት ፡ ነጥብ ፡ ነው

ቆይ ፡ ቆቆይ ፡ ቆቆይ ፡ ቆቆይ ፡ ቆይ ፡ እስቲ ፡ አሃ ፡ ቆይ
ቆይ ፡ ቆቆይ ፡ ቆቆይ ፡ ቆቆይ ፡ ቆይ ፡ እስቲ ፡ አሃ
ማነውስ ፡ ለጠላቱ ፡ ሕይወቱን ፡ የሚሰጠው
ስለ ፡ ፍቅር ፡ ብሎ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ የሚሞተው

ነፍሴ ፡ ያደላው ፡ ለእርሱ ፡ ነው (፪x)
ልቤ ፡ ያደላው ፡ ለእርሱ ፡ ነው (፫x)

የማያዳክመን ፡ ምርጫ ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ ፡ አረኩኝ
ኢየሱስን ፡ ላለውጠው ፡ በፊቱ ፡ ቃልን ፡ ገባሁኝ
አሃሃሃሃ ፡ በድካም ፡ በብርታታ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ልሆን ፡ ወሰንኩኝ
አሃሃሃ...