From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እግዚአብሔርን ሊሰሙ ለሚወዱ ትናገራለህ
ሊያዩህ ለሚሹ ለናፈቁ ትገለጣለህ
በቀናዋ መንገድ ሊሄዱ ለመረጡ
እስከ ፍጻሜው ትመራቸዋለህ
አዝ፦
ለሚጠሩህ ቅርብ ለሚጠሩህ ቅርብ
ለሚፈልጉህ ጌታ ትገኛለህ
ለሚጠሩህ አሁን ለሚጠሩህ ዛሬም
ለሚፈልጉህ ፈጥነህ ትገኛለህ
ከመቼውም ይልቅ አንተን እፈልጋለሁ
ሁሌ ወዳንተ ልጠጋ ወዳለሁ
ፍቅርህ ሰርጾ ውስጤ ገብቷል
ሌላው ነገር በፊቴ ቀልሎብኛል
ፍቅርህ ሰርጾ ውስጤ ገብቷል
ሌላው ነገር በፊቴ ቀልሎብኛል
በእውነትና በመንፈስ ለሚፈልጉህ
ሁሉን ነገር ትተው ለተከተሉህ
እንደ ቃልህ አንተ ትገኛለህ
ተዓምራትን በእነርሱ ታደርጋለህ
እንደ ቃልህ አንተ ትገኛለህ
ተዓምራትን በእነርሱ ታደርጋለህ
አዝ፦
ለሚጠሩህ ቅርብ ለሚጠሩህ ቅርብ
ለሚፈልጉህ ጌታ ትገኛለህ
ለሚጠሩህ አሁን ለሚጠሩህ ዛሬም
ለሚፈልጉህ ፈጥነህ ትገኛለህ
ቀድሞ ለአባቶቼ እንዳረክላቸው
በትውልድ መካከል እንዳከበርካቸው
ዛሬም በእኛ ዘመን ቅርብ ነህ
ማዳንህን አያለሁ ትሰራለህ
ዛሬም በእኛ ዘመን ቅርብ ነህ
ክንድህን አያለሁ ትሰራለህ
አዝ፦
ለሚጠሩህ ቅርብ ለሚጠሩህ ቅርብ
ለሚፈልጉህ ጌታ ትገኛለህ
ለሚጠሩህ አሁን ለሚጠሩህ ዛሬም
ለሚፈልጉህ ፈጥነህ ትገኛለህ
|