From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የናርዶስ ፡ ሽቶዬ ፡ የአልባስጥሮስ
መጓደጃዬ ፡ ውድ ፡ ኢየሱስ
ልቤ ፡ ከልብህ ፡ ጋር ፡ ተቆራኝቶ
መኖር ፡ ወደደ ፡ አንተን ፡ አግኝቶ (፪x)
አንተን ፡ አግኝቶ (፬x)
አዝ፦ ቅዱሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ የማውቀህ ፡ ከልጅነቴ
ንጉሡ ፡ እግዚአብሔር ፡ የምሻህ ፡ ከልጅነቴ
እርስቴም ፡ ተድላዬም ፡ ጥጋቤም
አንተ ፡ ነህ ፡ ማር ፡ እና ፡ ወተቴ (፭x)
የቆላ ፡ አበባ ፡ ፅጌረዳዬ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ውሎ ፡ መግቢያዬ
በማሰማሪያህ ፡ በታዛ ፡ ሥር
አንተን ፡ ሳመልክህ ፡ ውዬ ፡ ልደር (፭x)
ውዬ ፡ ልደር (፬x)
መጣሁኝ ፡ ወዳሳየኸኝ ፡ ውብ ፡ ሥፍራ
አየሁ ፡ የግርማህን ፡ ፀዳል ፡ ሲያበራ
ወዳጄ ፡ ለመሆኑ ፡ ሰው ፡ አወቀህ ፡ ወይ
ቁንጅናህ ፡ ለሀገር ፡ የሚተርፍ ፡ አይደል ፡ ወይ (፫x)
አዝ፦ ቅዱሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ የማውቀህ ፡ ከልጅነቴ
ንጉሡ ፡ እግዚአብሔር ፡ የምሻህ ፡ ከልጅነቴ
እርስቴም ፡ ተድላዬም ፡ ጥጋቤም
አንተ ፡ ነህ ፡ ማር ፡ እና ፡ ወተቴ (፭x)
ልቤ ፡ መልካምን ፡ ቅኔ ፡ አፈለቀ
ንጉሡን ፡ ጌታ ፡ እያደነቀ
ውበቱ ፡ ከአምራል ፡ ከሰው ፡ ይልቅ
የእኔማ ፡ ኢየሱስ ፡ ከብርቅም ፡ ብርቅ (፬x)
አዝ፦ ቅዱሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ የማውቀህ ፡ ከልጅነቴ
ንጉሡ ፡ እግዚአብሔር ፡ የምሻህ ፡ ከልጅነቴ
እርስቴም ፡ ተድላዬም ፡ ጥጋቤም
አንተ ፡ ነህ ፡ ማር ፡ እና ፡ ወተቴ (፱x)
|