From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እግዚአብሔር : አዋቂ : ነው : ስራውን : ይመዝናል
እንደ : ሰው : እንደሰማ : እንዳየ : መች : ይፈርዳል
ከእኔ : ይልቅ : ስለ : እኔ : እርሱ : ያስባልና
(ሃሳቤን : በእርሱ : ጣልኩት : አያሳፍርምና)
ጌታዬ : አዋቂ : ነው : (የሚያደርገውን : ያውቃል)2
ከቶ : አልናወጥም : (ልቤም : በእርሱ : አርፏል)2
ጌታዬ : አዋቂ : ነው : (የሚያደርገውን : ያውቃል)2
ነገርን : በጊዜው : (ውብ : አርጎ : ይሰራል)2
ከማስበው : ያሰበልኝ : ይበልጣል
ከማቅደው : ያቀደልኝ : ይበልጣል
እኔ : አላውቅም : እግዚአብሔር : ያውቃል (2)
(እግዚአብሔር : ያውቃል)3
ልቤም : በእርሱ : አርፏል
ከእኔ : ሃሳብ : ይልቅ : (የአንተ : ሃሳብ : ይበልጣል)2
እኔ : የማላየውን : (አይንህ : ዘልቆ : ያያል)2
ጨለማ : በአንተ : ዘንድ : (አይጨልምምና)2
አሜን : ብያለሁኝ : የአንተ : ሃሳብ : ይጽና
የአንተ : ምክር : ይጽና
እግዚአብሔር : አዋቂ : ነው : ስራውን : ይመዝናል
እንደ :ሰው : እንደሰማ : እንዳየ : መች : ይፈርዳል
ከእኔ : ይልቅ : ስለ : እኔ : እርሱ : ያስባልና
(ሃሳቤን : በእርሱ : ጣልኩት : አያሳፍርምና)2
|