From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በቃልህ ፡ ትእዛዝ ፡ በስልጣንህ ፡ በትር
ሁሉን ፡ ትገዛለህ ፡ ላንተ ፡ ይሁን ፡ ክብር
ከክብር ፡ ጋር ፡ ስፍራን ፡ በቀኝህ ፡ ሰጠኸኝ
ምን ፡ ቢለፋ ፡ ቢጥር ፡ ጠላቴ ፡ አያገኘኝ
አዝ፦ ልነሳ ፡ ላመስግን ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ከእግርህ ፡ ስር
ልሰዋ ፡ ምስጋና ፡ ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፪x)
ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፬x)
በሚታየው ፡ አልለውጥህም
በሁኔታ ፡ አልገምትህም
ቢመሽም ፡ ቢነጋም ፡ አውቃለሁ
አንተን ፡ ለማመስገን ፡ እቆማለሁ ፡ ፪x
አዝ፦ ልነሳ ፡ ላመስግን ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ከእግርህ ፡ ስር
ልሰዋ ፡ ምስጋና ፡ ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፪x)
ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፬x)
ዘመኔን ፡ በክብርህ ፡ አስዋብከው ፡ ከአውሬና ፡ ከተኩላው ፡ አድነህ
ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ መራኸኝ ፡ በእጅህ ፡ እጄን ፡ ይዘህ
ታሪኬ ፡ ሆንክልኝ ፡ ትምክቴ ፡ ትርጉም ፡ ለሕይወቴ
አመሰግናለሁ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ኢየሱስ ፡ መድኃኒቴ (፪x)
አዝ፦ ልነሳ ፡ ላመስግን ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ከእግርህ ፡ ስር
ልሰዋ ፡ ምስጋና ፡ ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፪x)
ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፬x)
እንደ ፡ ባለማዕረግ ፡ ተቀብለኸኛል
እቅፍህ ፡ ይደላል ፡ ተመችተኸኛል
የሕይወቴ ፡ እርካታ ፡ አንተ ፡ ከሆንክልኝ
ዓይኔ ፡ ሌላ ፡ አያይም ፡ ምን ፡ ሊፈይድልኝ (፪x)
አዝ፦ ልነሳ ፡ ላመስግን ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ከእግርህ ፡ ስር
ልሰዋ ፡ ምስጋና ፡ ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፪x)
ክብር ፡ የሚገባህ ፡ ነህና (፬x)
|