From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ ባማረ ፡ ምስጋና (፪x)
እሰዋልሃለሁ ፡ ይገባሃልና (፪x)
ገናና ፡ ገናና ፡ ነህና (፬x)
እታመንሃለሁ ፡ ትምክህቴ ፡ ነህ ፡ ለኔ
መልካምነት ፡ ህን ፡ አይቻለሁ ፡ ባይኔ
የምስጋናዬም ፡ ቃል ፡ ይውጣና ፡ ይሰማ
ገና ፡ እጨምራለሁ ፡ ይህ ፡ ካረካህማ
አዝ፦ በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ ባማረ ፡ ምስጋና (፪x)
እሰዋልሃለሁ ፡ ይገባሃልና (፪x)
ገናና ፡ ገናና ፡ ነህና (፬x)
ሞገሴ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ በጥላህ ፡ አርፌአለሁ
ላመልክህ ፡ ይገባኛል ፡ ፍቅርህን ፡ ቀምሻለሁ
ኃያል ፡ ነህ ፡ ክንደ ፡ ብርቱ ፡ ማን ፡ እንተን ፡ ይጋፋና
ዙፋንህ ፡ የጸና ፡ ነው ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ባለዝና (፪x)
አዝ፦ በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ ባማረ ፡ ምስጋና (፪x)
እሰዋልሃለሁ ፡ ይገባሃልና (፪x)
አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ነህና (፬x)
አንተን ፡ ይዤ ፡ አላፈርኩም ፡ አታሳፍርምና
ሁሉን ፡ አሻግረኸኛል ፡ ከበህ ፡ ከፊት ፡ ከኋላ
እግሬን ፡ በከፍታ ፡ ላይ ፡ አጽንተህ ፡ አቁመሃል
ገናና ፡ ነህ ፡ እያልኩኝ ፡ ባመልክህ ፡ ያንስብሃል (፪x)
ገናና ፡ ገናና ፡ ነህና (፰x)
|