From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ሁሉን ፡ ያዘጋጀው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
የለም ፡ አንዳች ፡ ከኔ ፡ ብዬ ፡ ምለው
በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ የሆነው
በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ የሆነው (፪x)
ጽድቅ ፡ ነው ፡ ለኔስ ፡ ጌታዬ ፡ ጽድቅ ፡ ሆኖ ፡ የተቆጠረልኝ
ጠላቴን ፡ ድባቅ ፡ የመታው ፡ ከእግሬ ፡ ስር ፡ ፈጥኖ ፡ የጣለልኝ
ላክብረው ፡ ሥሙን ፡ በዜማ ፡ ቅኔዬን ፡ አሰካክቼ
አልችልም ፡ ዝም ፡ ለማለት ፡ ልባርከው ፡ እጄን ፡ አንስቼ
አዝ፦ ሁሉን ፡ ያዘጋጀው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
የለም ፡ አንዳች ፡ ከኔ ፡ ብዬ ፡ ምለው
በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ የሆነው
በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ የሆነው (፪x)
ተዓምርን ፡ ሰርቶ ፡ ያዳነኝ ፡ ሞቴንም ፡ በሞት ፡ የሻረው
ትንሳዔን ፡ ለኔ ፡ ያወጀ ፡ ታሪኬን ፡ የለዋወጠው
ምስኪኑን ፡ ከትቢያ ፡ አንስቶ ፡ በድል ፡ ላይ ፡ ድል ፡ የሚሰጠው
እንዲህ ፡ ነው ፡ የታመንኩበት ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ የምለው
አዝ፦ ሁሉን ፡ ያዘጋጀው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
የለም ፡ አንዳች ፡ ከኔ ፡ ብዬ ፡ ምለው
በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ የሆነው
በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ የሆነው (፪x)
የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ ፡ ገንኖልኝ ፡ በላዬ
ጨለማዬም ፡ በራ ፡ ቆምኩኝ ፡ ቀና ፡ ብዬ (፪x)
ተከፋፈተልኝ ፡ የሰማዩም ፡ ደጃፍ
አምላኬ ፡ ሲረዳኝ ፡ አየሁ ፡ አዲስ ፡ ምዕራፍ (፬x)
አዝ፦ ሁሉን ፡ ያዘጋጀው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
የለም ፡ አንዳች ፡ ከኔ ፡ ብዬ ፡ ምለው
በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ የሆነው
በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ የሆነው (፪x)
|