From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ምህረትህ ፡ አዲስ ፡ ነው
ታማኝነትህም ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ምህረትህ ፡ አዲስ ፡ ነው
ታማኝነትህም ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x)
ጉልበት ፡ ሲዝል ፡ አቅም ፡ ጠፍቶ ፡ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ሲታጣ
ማን ፡ እንዳንተ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ አለሁ ፡ ባይ ፡ መከታ
ቢደገፉት ፡ እሚያኮራ ፡ ቢታመኑት ፡ ታማኝ
አይገኝም ፡ ካንተ ፡ በቀር ፡ በምድርም ፡ በሰማይ
አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x)
ጠላት ፡ ቢዋዥ ፡ በኃይልህ ፡ ላይ ፡ ትርፉ ፡ ድካሙ ፡ ነው
ያልከው ፡ አይቀር ፡ ይፈጸማል ፡ ምክርህ ፡ የጸና ፡ ነው
ትላንትናን ፡ እንደሰራህ ፡ ዛሬም ፡ ትሰራለህ ፡
ክንድህ ፡ አይዝል ፡ አስተማማኝ ፡ ሁልጊዜም ፡ ታማኝ ፡ ነህ
አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x)
አንተን ፡ ይዞ ፡ ማን ፡ አፈረ ፡ ካንተ ፡ የተጠጋ
አድነኸው ፡ አማረበት ፡ ከጠላት ፡ መንጋጋ
ታሪክ ፡ መስራት ፡ ልማድህ ፡ ነው ፡ ክንድህ ፡ አይታክትም
እርስትህን ፡ አሳልፈህ ፡ ለጠላት ፡ አትሰጥም
አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x)
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ምህረትህ ፡ አዲስ ፡ ነው
ታማኝነትህም ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
አዝ፦ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ታማኝ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፬x)
በዙሪያዬ ፡ ጋሻ ፡ የእሳት ፡ ቅጥር ፡ ሆነ
ከጥፋት ፡ ማምለጫ ፡ ኢየሱስ ፡ አለቴ ፡ ነህ
በለመለመ ፡ መስክ ፡ መምራት ፡ ስታውቅበት
የዘላለም ፡ ብርሃን ፡ ቀን ፡ ለጨለመበት
የዘላለም ፡ ብርሃን ፡ ነህ ፡ የዘላለም ፡ ብርሃን (፰x)
|