ማንም : የለኝ : ከኢየሱስ : በላይ (Manem yelegn keyesus belay) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
(Kalkidan Tilahun)

Lyrics.jpg


(Volume)

አልበም
(1)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቃልኪዳን ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Kalkidan Tilahun)

ማንም ሊፈታው አይችልም
ነገሬን ጉዳዬን ጌታ ሆይ
ማንም ሊፈታው አይችልም
ነገሬን ጉዳዬን ጌታ ሆይ

አንተ ጋር መጣለሁ ይዤው ነገሬን ገዳዬን
አንተዉ ጋር መጣለሁ ይዤው ነገሬን ገዳዬን

ፈቺ ነህ ጌታ ፈቺ ነህ
ፈቺ ነህ አንተ ፈቺ ነህ
ፈቺ ነህ ጌታ ፈቺ ነህ
ፈቺ ነህ አንተ ፈቺ ነህ

ፍቅሩ ተፈትኖ ወርቅ ሆኖ ተገኝቷል
በመከራ አልፎ ነፍሱን ለኔ ሰጧል
እራሱን አዋርዶ ፍቅሩን አሳይቷል
ከፍቅሮችም በላይ የእሱ ፍቅር በልጧል

ማንም የለኝ ከኢየሱስ በላይ
ስመላለስ በዚች ምድር ላይ
ነፍሱን ለኔ ቤዛ ያረገው
እውነተኛ ወዳጄ እሱ ነው

ለህይወቴ ፍቺ ትርጉምን የሰጠው
ኑሮዬን አጣፍጦ እንዲህ ያደረገው
በእውነተኛ ፍቅሩ ያዳነኝ የመራኝ
ከኢየሱስ የሚበልጥ ለእኔ ማንም የለኝ

ማንም የለኝ………..

ለክፎዎችም ቸር የሀጢያተኛው ወዳጅ
ከጥፋት ሚመልስ ለሰዎች የሚበጅ
ልብን የሚነካ ንግግሩ ጣፋጭ
እውነተኛ መሲሕ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ

ማንም የለኝ……..

እኔ መኖር አልችል ስምህን ሳልጠራ
አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ
እኔ መዋል አልችል ስምህን ሳልጠራ
አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ
እኔ ማደር አልችል ስምህን ሳልጠራ
አንተ በእኔ ህይወት አለህ ትልቅ ስፍራ
እኔ መዋል አልችል ስምህን ሳልጠራ
አንተ በህይወቴ አለህ ትልቅ ስፍራ

ያለምንም ነገር መኖር እችላለሁ
ደግሞም አይገርመኝም ኖሬ አይቼዋለሁ
ግን ያላንተ ጌታ እንዴት እኖራለሁ
ግን ያላንተ ኢየሱስ እንዴት እኖራለሁ