ጣልቃ ሲገባ (Talka Sigeba) - ህሊና ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ህሊና ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(linurilih)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 7:51
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

ጣልቃ ሲገባ

እግዚአብሄር ጣልቃ ሲገባ እጁ ሲነሳ
ማነው ሚረዳ ማነው ሚያስረዳ
ማነው ሚረዳ ማነው ሚያስረዳ
እግዚአብሄር ጣልቃ ሲገባ እጁ ሲሰራ
ማነው ሚረዳ ማነው ሚያስረዳ
ማነው ሚረዳ ማነው ሚያስረዳ
የዘመናትን ጥያቄ በአንዲት ለሊት
የእድሜ ዘመን ቋጠሮ በአንድ ሰከንድ
አየን ሲፈታ አየን ሲፈታ
የዘመናትን ጥያቄ በአንዲት ለሊት
የእድሜ ዘመን ቋጠሮ በአንድ ሰከንድ
አየን ሲፈታ አየን ሲፈታ
አየን ሲፈታ አየን ሲፈታ

ርህራሄህ ቸርነትህ አያልቅምና አያልቅምና
የሰው ልጆች ሁሉ መጡ ወዳንተ
እረፍት ፍለጋ እረፍት ፍለጋ
ርህራሄህ ምህረትህ አያልቅምና አያልቅምና
ፍጥረት ሁሉ መጡ ወዳንተ
ህይወት ፍለጋ ህይወት ፍለጋ
የሰራዊት አምላክ ዛሬም አንተ ስራ
በአምላክረት በክብርህ ፊትህ ያብራ
ፊትህ ያብራ ፊትህ ያብራ
ጣልቃ ግባ ጣልቃ ግባ
የሰራዊት አምላክ ዛሬም አንተ ስራ
በአምላክረት በክብርህ ፊትህ ያብራ
ፊትህ ያብራ ፊትህ ያብራ
ጣልቃ ግባ ጣልቃ ግባ

ይህቺ እማ የእግዚአብሔር ጣት ናት
ይህቺ እማ የእግዚአብሔር ክንድ
የሚያስብልን ተአምራት ስታደርግ በምህረትህ
ሰምተው መጡ ዙሪያዬ ያሉ ሁሉ
አላዛሬን ሊጎበኙ
የሸተተው የገነዝኩት ቆሞ ሲሄድ በድንገት
ይህቺ እማ የእግዚአብሔር ጣት ናት
ይህቺ እማ የእግዚአብሔር ክንድ
የሚያስብልን ተአምራት ስታደርግ በምህረትህ
ሰምተው መጡ ዙሪያዬ ያሉ ሁሉ
አላዛሬን ሊጎበኙ
የሸተተው የገነዝኩት ቆሞ ሲሄድ በድንገት
ሙታን የሚታዘዙለት ስላስነሳው
ሙታን አቤት የሚሉት ስለጠራው
ሙታን የሚታዘዙለት ስላስነሳው
ሙታን አቤት የሚሉት ስለጠራው

ርህራሄህ ቸርነትህ አያልቅምና አያልቅምና
የሰው ልጆች ሁሉ መጡ ወዳንተ
እረፍት ፍለጋ እረፍት ፍለጋ
የሰራዊት አምላክ ዛሬም አንተ ስራ
በአምላክረት በክብርህ ፊትህ ያብራ
ፊትህ ያብራ ፊትህ ያብራ
ጣልቃ ግባ ጣልቃ ግባ

ከባርነት ከእድሜ ልክ እስር
በአንድ ቀን ዮሴፍ ሲነግስ
በእኔ እርዳታ በእኔ ማገዝ
እዚህ ደርሳል ማንስ ሊል
የማንም እጅ ያልተባበረበት
እግዚአብሔር ብቻውን ያለበት
ሆኖ ፀና ግሩም ተአምር
እስከ ዛሬ ነው ምስክር
ከልጅነት የጠራውን ተማምኖበት
ህልሙን የሰጠውን ጌታ ተወራርዶበት
ከልጅነት የጠራውን ተማምኖበት
ህልሙን የሰጠውን ጌታ ተወራርዶበት

የህይወቴ በሮች ሁሉ ክፍት ናቸው ለንጉሱ
ለንጉሱ በሮች ይከፈቱ ለንጉሱ ደጆች ይከፈቱ
የህይወቴ በሮች ሁሉ ክፍት ናቸው ለንጉሱ
ለንጉሱ በሮች ይከፈቱ ለንጉሱ ደጆች ይከፈቱ