መንገዴ ነህ (Mengede Neh) - ህሊና ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ህሊና ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(linurilih)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

መንገዴ ነህ

መፍትሄ ሲጠፉኝ መልሱ ሳይገባኝ
አይደለም ምጠራህ መውጫ ሲጠፋኝ
ሲነጋ ሲመሽ ድምፅህን መስማት
ተለማምጃለሁ ፊትህን መሻት
መፍትሄ ሲጠፉኝ መልሱ ሳይገባኝ
አይደለም ምጠራህ መውጫ ሲጠፋኝ
ሲነጋ ሲመሽ ድምፅህን መስማት
ተለማምጃለሁ ፊትህን መሻት

መንገዴ ነህ አንተ ምርጫዬ
አማክርሀለሁ ጉዳዬን
ሌላስ የት ልሂድ ካንተ ውጪ
አለም የሚያስተምረው አይገባኝ
መንገዴ ነህ አንተ ምርጫዬ
አማክርሀለሁ ጉዳዬን
ሌላስ የት ልሂድ ካንተ ውጪ
አለም የሚያስተምረው አይገባኝ

የራሴ አይደለሁም ከፍሎልኛል ዋጋውን
በማይረክስ ማይጠፉው በከበረው ደሙ
ታዲያ እንዴ ምን ይባላል ህይወቴ ነው ስለው
ከመፈጠሬ በፊት መሰዋት ለሆነው
የራሴ አይደለሁም ከፍሎልኛል ዋጋውን
በማይረክስ ማይጠፉው በከበረው ደሙ
ታዲያ እንዴ ምን ይባላል ህይወቴ ነው ስለው
ከመፈጠሬ በፊት መሰዋት ለሆነው

ያበጃጀኸኝ በራስህ አምሳል
እፍ ያልክብኝ ቅዱስ መንፈስህን
ማደርያህ እንድሆን የፍቅርህ አጋር
ቀድመህ ለየኸኝ ከፍጥረታት
መልአክቶቹ እንኳን ተገርመው
ሲመራመሩ የሰውን ልጅ አይተው
ምነኛ ይሆን የተወደድነው
ወልድ ከዙፉንህ ፈቅደህ የወረድከው
እውነትም ህይወት መንገድ ነኝ ያልከው
የአብን ፍቅር አንተ ተረከው
ለኔም ተስፉዬ እረፍቴ የሆንከው
እድሜ ዘመኔ ሁሉ ያንተ ነው

መንገዴ ነህ አንተ ምርጫዬ
አማክርሀለሁ ጉዳዬን
ሌላስ የት ልሂድ ካንተ ውጪ
አለም የሚያስተምረው አይገባኝ

ሸክላው በሰሪው እጅ ውስጥ እንዳለው
ነው የኔ ህይወት ባንተ የተቃኘው
ከልጅነቴ በእቅፍህ አለሁ
እየመራኸኝ ፊትህን እያየሁ
መካሪዬ ነህ መሸሸጊያዬ
ሁሉን ምነግርህ ሚስጥረኛዬ
የግል የራሴ መንፈስ ቅዱሴ
ብቸኛ ምርጫ ነህ አንተ ለኔ

መንገዴ ነህ አንተ ምርጫዬ
አማክርሀለሁ ጉዳዬን
ሌላስ የት ልሂድ ካንተ ውጪ
አለም የሚያስተምረው አይገባኝ
መንገዴ ነህ አንተ ምርጫዬ
አማክርሀለሁ ጉዳዬን
ሌላስ የት ልሂድ ካንተ ውጪ
አለም የሚያስተምረው አይገባኝ