From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
መንገድን ልጥረግልህ
ዘወትር ላጥንልህ በየልት ላጥንልህ
ላመቻች የልቤን ዙፋን
ንጉስ ሆይ እረፍ በእኔ ላይ
መንፈስ ቅዱስ ስፈን በእኔ ላይ
ላስተናግድ መለኮትን
ደርሶ የለ ቀጠሮዋችን ደርሶ የለ ቀጠሮዋችን
እንግዳዬ እንግዳዬ
ከሩቅ ሰማሁኝ ኮቴህን እንግዳዬ
ቤቴን አወደው ሽታህ እንግዳዬ
ኢየሱሴ ኢየሱሴ
ለሊት ሰማሁኝ ድምፅህን ኢየሱሴ
ይኸው መጣሁኝ ስትል ኢየሱሴ
ናፍቆቴ ናፍቆቴ ና ክረም በቤቴ
ና ሰምብት በቤቴ ናፍቆቴ
ረድኤቴ መልህቄ ና ሰምብት በቤቴ
አልለቅህም ክረም በቤቴ መድሀኒቴ
በለሊት ሳሰላስልህ
በእንቅልፌም ደግሞ ሳልምህ
ፍቅርህ ልቤን ጎትቶት
ስጋዬ እንኳን አንተን ተርቦት
ሳሰናዳ አእምሮዬን
ስጠብቅህ እጅግ በጉጉት
መጣህልኝ እንደ ቃልህ
አገኘኸኝ እንደማልከው
በመንፈስ ቅዱስ ሀሴት አድርጌ
ፊትህን ሳየው ተመኘሁ ዛሬ
ምነው እንደ ሄኖክ ብሻገረው
እጄን ይዘኸው ወደዛኛው
ምነው እንደ ሄኖክ ብሻገረው
እጄን ይዘኸው ወደዛኛው
እንግዳዬ እንግዳዬ
ከሩቅ ሰማሁኝ ኮቴህን እንግዳዬ
ቤቴን አወደው ሽታህ እንግዳዬ
ኢየሱሴ ኢየሱስዬ
ለሊት ሰማሁኝ ድምፅህን ኢየሱሴ
ይኸው መጣሁኝ ስትል ኢየሱሴ
ጠረንህ ቤቴን አውዶት
ህልውናህ አጥንቴን ተሰምቶት
የክብርህ ደመና ከቦኝ
ሙቀትህ ዙሪያዬን አቅፎኝ
በቅድስተ ቅዱሳንህ ውስጥ
ራሴን አገኘሁት ሳመልክ
ከቅዱሳን ጉባኤ ጋራ
በመንፈሴ ምስጋናን ሳሰማ
መልአክቶቹም ሲቀኙልህ
እኔም አጅቤ ሳለቅስ ሳዜም
የመፈጠሬን ትርጉም አግንቼ
ልቀር ጎጎሁኝ ለዘላለሜ
የመፈጠሬን ትርጉም አግንቼ
ልቀር ጎጎሁኝ ለዘላለሜ
መልአክቶቹም ሲቀኙልህ
እኔም አጅቤ ሳለቅስ ሳዜም
የመፈጠሬን ትርጉም አግንቼ
ልቀር ጎጎሁኝ ለዘላለሜ
የመፈጠሬን ትርጉም አግንቼ
ልቀር ጎጎሁኝ ለዘላለሜ
እንግዳዬ እንግዳዬ
ከሩቅ ሰማሁኝ ኮቴህን እንግዳዬ
ቤቴን አወደው መአዛህ እንግዳዬ
ኢየሱሴ ኢየሱሴ
ለሊት ሰማሁኝ ድምፅህን ኢየሱሴ
ይኸው መጣሁኝ ስትል ኢየሱሴ
ናፍቆቴ ናፍቆቴ ና ክረም በቤቴ
ና ሰምብት በቤቴ ናፍቆቴ ናፍቆቴ
ረድኤቴ መልህቄ ና ሰምብት በቤቴ
አልለቅህም ክረም በቤቴ መድሀኒቴ
አቤት ስወድህ ስቀርብህ ስወድህ
መቼም አልጠግብህ አልጠግብህ አልጠግብህ
ውዴ ስወድህ ስቀርብህ ስወድህ
ለዘላለም አልጠግብህ አልጠግብህ አልጠግብህ
አቤት ስወድህ ስቀርብህ ስወድህ
መቼም አልጠግብህ አልጠግብህ አልጠግብህ
ውዴ ስቀርብህ ስወድህ ስወድህ
ለዘላለም አልጠግብህ አልጠግብህ አልጠግብህ
|