ምነው (Menew) - ህሊና ፡ ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Hillina Kassahun 2.jpg


(2)

አልበም
(Egziyabeher Tilik)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፯ (2014)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ፡ ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

ምነው (Track 10)

(ምነው ምነው ምነው ምነው እየሱስ እያለ ልብህ ያዘነው
ምነው ምነው ምነው ምነው እግዚአብሔር እያለ ልብሽ ያዘነው)

ምነው ምነው ምነው ምነው እየሱስ እያለ ልብህ ያዘነው
ምነው ምነው ምነው ምነው እግዚአብሔር እያለ ልብሽ ያዘነው

ትዝ አይልህም ወይ ከየት እንዳወጣህ.. አሀሀ
ከተደፋፈነው ከድቅድቅ ጨለማ … አሀሀ
ትርፍ ዋጋ የለውም አበቃለት በቃ ..አሀሀ
በተባለው ሰፈር ታሪክህን ሰራ …አሀሀ
የተከመረውን ትልቁን ተራራ..አሀሀ
በአንድ ቃል እንዳልነበር አፈረሰው እና..አሀሀ
ማያልቀው እንባህን ከአይኞችህ ላይ
ጌታ አብሶልህ አላየህም ወይ
ዝናብ ከላይ ወርዶ እንዳይመለስ
ምድርና መላዋን ሳያረሰርስ
እንዲሁ እኮ ነው የእግዚአብሔር ቃል
ተፈፅሞ አየን አንዳች ሳትቀር (2x)

(ኦሆ አሆሆሆ አሀሀሀ)

ቆም ብለህ ወደላይ ብታይ ለደቂቃ .. አሀሀ
ሳቅልኝ ይልሀል የሰራዊት ጌታ .. አሀሀ
አታውቀውም ወይ የልቤን ደስታ.. አሀሀ
አንተ ስትስቅልኝ ነፍስህም ሲረካ.. አሀሀ
የድሮውን ትተህ በእኔ ስትመካ .. አሀሀ፤
በሙሉ መንፈስህ በሙሉ ሀሳብህ
አምነኸኝ ስትኖር ልቤን አስደሰትክ
ዝናብ ከላይ ወርዶ እንዳይመለስ
ምድርና መላዋን ሳያረሰርስ
እንዲሁ እኮ ነው የምነግርህ ቃል
ፀንተህ ስትጠብቀው ፍፃሜው አይቀር (2x)

ምነው ምነው ምነው ምነው እየሱስ እያለ ልብህ ያዘነው
ምነው ምነው ምነው ምነው እግዚአብሔር እያለ ልብሽ ያዘነው (3x)