እግዚአብሔር አለቴ (Egziabher Alete) - ህሊና ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ህሊና ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Lyrics.jpg


(3)

ልኑርልህ
(Linurelih)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 7:49
ጸሐፊ (Writer): ህሊና ፡ ካሳሁን
(Hillina Kassahun
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

እግዚአብሔር/3 አለቴ አለቴ
እየሱስ/3 መንገዴ ብቸኛ መንገዴ

ቀን ወጣልኝ ለኔ ቀን ወጣልኝ ለኔ አንተን በማመኔ
ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደንቅ ብርሃን በመተላለፌ
ቀን ወጣልኝ ለኔ ቀን ወጣልኝ ለኔ አንተን በማወቄ
ከጨለማው መንግስት ወደ ብርሃኑ በመተላለፌ

ገመዴ ባማረ ስፍራ ወድቃ
አይኖችህ እኔን ተመልክታ
እንከኔን ካላዬ አራግፈህ
እዳዬን በቀራንዮ ከፍለህ

ወደድክ አንተ የራስህ ልታረገኝ ንብረትህ
የፍቅርህ መገለጫ የኪዳንህ አጋር ኦሆሆሆ

እንደኔ ማነው የተጎበኘው
ከሰማይት ጠል ነፍሱ የጠገበው/2

እግዚአብሔር/3 አለቴ አለቴ
እየሱስ/3 መንገዴ ብቸኛ መንገዴ

ቀን ወጣልኝ ለኔ ቀን ወጣልኝ ለኔ አንተን በማመኔ
ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደንቅ ብርሃን በመተላለፌ
ቀን ወጣልኝ ለኔ ቀን ወጣልኝ ለኔ አንተን በማወቄ
ከጨለማው መንግስት ወደ ብርሃኑ በመተላለፌ

ባለቤቷ እጥታ ስትባዝን
የህይወቷን ትርጉም ስትፈልግ
የጨለማው ገዢ አወሯት
ወደ እሳት ባህሩ እየነዳት

አፈረስከው ቅጥሩን የዘመናት ዕቅዱን
ድህነት ሆነ ለነፍሴ መርዶ ደግሞ ለጠላቴ ኦሆሆሆ

ከመንጋጋው ውስጥ ፈልቅቀህ አውጥተህ
በህይወት ኑሪ አልከኝ ክብርህን አልብሰህ

ዛሬማ
ይፈሳል ይፈሳል ቅዱሱ መንፈስህ
አይሎ በሕይወቴ ያንተ መንግስትህ
ይፈሳል እንደ ወንዝ በነፃ መንፈስህ
ወርሶት ማንነቴን የክብርህ ግዛትህ

እግዚአብሔር/3 አለቴ አለቴ
እየሱስ/3 መንገዴ ብቸኛ መንገዴ

ቀን ወጣልኝ ለኔ ቀን ወጣልኝ ለኔ አንተን በማመኔ
ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደንቅ ብርሃን በመተላለፌ
ቀን ወጣልኝ ለኔ ቀን ወጣልኝ ለኔ አንተን በማወቄ
ከጨለማው መንግስት ወደ ብርሃኑ በመተላለፌ