በረከቴ (Berekete) - ህሊና ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ህሊና ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(linurilih)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 7:43
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

በረከቴ

እኔ የምሻው በረከት (ኦ)
የውስጥ የልቤ ጥማት (አ)
የሁሉ ነገሬ መልስ
መንፈስ ቅዱስ መገኘትህ
የእግዚአብሄር ልጅ መገኘትህ
በቤቴ ውስጥ መገኘትህ
በመውጣቴ አብሮነትህ
በመግባቴ አብሮነትህ
እኔ የምሻው በረከት (ኦ)
የውስጥ የልቤ ጥማት (አዋ)
የሁሉ ነገሬ መልስ
መንፈስ ቅዱስ መገኘትህ
የእግዚአብሄር ልጅ መገኘትህ
በጎዳዬ መገኘትህ
በመውጣቴ አብሮነትህ
በመግባቴ አብሮነትህ

በእውነቱ አንተ አይደለህ የበረከት ትርጉሙ
በእውነት አንተ ብቻ የበረከት መሰረት
በእውነቱ አንተ አይደለህ የበረከት ትርጉሙ
በእውነት አንተ ብቻ የበረከት መሰረት
የሰው ልጆች ሁሉ ስኬት
ከሀሳብህ ጋር መስማማት
የሰው ልጆች ሁሉ ስኬት
በፈቃድህ ስር መገዛት
የሰው ልጆች ሁሉ ስኬት
አንዱን ልጅህን በእውነት ማመን
የሰው ልጆች ሁሉ ስኬት
ከሀሳብህ ስር መገዛት

በረከቴ በረከቴ በረከቴ አንተ ነህ እርስቴ
ሽልማቴ ሽልማቴ ሽልማቴ አንተ ነህ ድርሻዬ
በረከቴ በረከቴ በረከቴ አንተ ነህ እንቁዬ
መድሀኒቴ መድሀኒቴ መድሀኒቴ አንተ ነህ እርካታዬ

እንደ ሌዋውያን እንደ ካህናቱ
የእለት ክፍያዬ ድርሻና ደዋዜ
አንተው ነህ ጌታዬ
ድንኳን ውስጥ አድራለሁ ይቅርብኝ ማረፍያ
ነፍሴ አትኩራለች በጉጉት ጥበቃ
ያንተን ውብ ከተማ
እንደ ሌዋውያን እንደ ካህናቱ
የእለት ክፍያዬ ድርሻና ደዋዜ
አንተው ነህ ጌታዬ
ድንኳን ውስጥ አድራለሁ ይቅርብኝ ማረፍያ
ነፍሴ አትኩራለች በጉጉት ጥበቃ
ያንተን ውብ ከተማ
እጅህ የሰራትን መሰረትዋ የፀና
ዙፋንህ ያለበት የህይወት ወንዝ ውሀ
ሁሉም የሚረካበት ባንተ ህልውና
ያኔ ነው ሽልማት አክሊሌን ስደፋ
እጅህ የሰራትን መሰረትዋ የፀና
ዙፋንህ ያለበት የህይወት ወንዝ ውሀ
ሁሉም የሚረካበት ባንተ ህልውና
ያኔ ነው ሽልማት አክሊሌን ስደፋ

በረከቴ በረከቴ በረከቴ አንተ ነህ እርስቴ
ሽልማቴ ሽልማቴ ሽልማቴ አንተ ነህ ድርሻዬ
በረከቴ በረከቴ በረከቴ አንተ ነህ እንቁዬ
መድሀኒቴ መድሀኒቴ መድሀኒቴ አንተ ነህ እርካታዬ

ምናየው ሁሉ እንደ ጢስ ያልፋል
ሰማይና ምድር ይጠቀለላል
ትንብት ይሻራል ህልምም ይሻራል
ህያው ቃሉ ግን ዘላለም ይኖራል
ምናየው ሁሉ እንደ ጢስ ያልፋል
ሰማይና ምድር ይጠቀለላል
ትንብት ይሻራል ህልምም ይሻራል
ህያው ቃሉ ግን ዘላለም ይኖራል

ህያው ቃሉ ህያው ቃሉ ህያው ቃሉ
ኢየሱስ እራሱ ነው
ህያው ቃሉ ህያው ቃሉ ህያዉ ቃሉ
ኢየሱስ እራሱ
በረከቱ በረከቱ በረከቱ
ኢየሱስ እራሱ ነው
በረከቱ በረከቱ በረከቱ
ኢየሱስ እራሱ