አልለምደውም (Alemdewem) - ህሊና ካሳሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ህሊና ካሳሁን
(Hillina Kassahun)

Lyrics.jpg


(3)

አልበም
(linurilih)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 7:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የህሊና ካሳሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Hillina Kassahun)

አልለምደውም

ኢየሱስ ኢየሱስ
እግዚአብሄር ሰው ሆኖ ከዙፉኑ መውረዱ
ዛሬም ትኩስ
ይሄን ስጋ ለብሶ ራሱን ማዋረዱ
ዛሬም ትኩስ
ሞትና ትንሳኤው ዛሬም ትኩስ
የፈሰሰው ደሙ ዛሬም ትኩስ
የመስቀል ትግሉ ዛሬም ትኩስ
በእኔ ውስጥ ማደሩ ዛሬም ትኩስ

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
አልለምደውም አልንቀውም
አልረሳውም አላቀለውም
አልለምደውም አልንቀውም
አልረሳውም አላቀለውም
ተአምር ነው ተአምር ነው ተአምር ነው
የሄድክበት ርቀት እርቅን ለመፈጸም
ተአምር ነው
ፍቅርህን ለመግለጽ መንፈስህን ለማፍሰስ
ተአምር ነው
ተአምር ነው ተአምር ነው ተአምር ነው
የሄድክበት ርቀት እርቅን ለመፈጸም
ተአምር ነው
ፍቅርህን ለመግለጽ መንፈስህን ለማፍሰስ
ተአምር ነው

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
አልለምደውም አልንቀውም
አልረሳውም አላቀለውም
አልለምደውም አልንቀውም
አልረሳውም አላቀለውም

ገና አለማት ሳይፈጠር በራስህ ውስጥ
ያለ ነውር ያለ እንከን
ንጹሕ አድርገህ በአብ ፊት ያቀረብከን
አንዲች ሀጥያት እንኳን ሳትሰራ
መሰዋትነትህን ቀድመህ ያፀናህ
ጊዜው ሲደርስ የትግሉ
አይንህን አትኩረህ ወደ መስቀሉ
ፍንክች እንኳን ሳትል ቀኝና ግራ
መራራውን ጽዎ ለአንዴ የጠጣህ

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
አልለምደውም አልንቀውም
አልረሳውም አላቀለውም
አልለምደውም አልንቀውም
አልረሳውም አላቀለውም

በአብ ቀኝ በራስህ ውስጥ አስቀምጠህ
የልጅነት መብትን ስልጣን
አባ ምልበት ድፍረትን አጎናፅፈህ
ወደ ፀጋህ ዙፋን ስር በነጻነት
እንድቀርብ ሆነልኝ ክብርህ ባለበት
ዛሬም በፀጋህ ስመላለስ
እባብና ጊንጡን እየረጋገጥኩ
አውቃለሁ አንዳችም ከእኔ እንዳልሆነ
ከሞት ያስነሳህ መንፈስ በእኔ እንዳደረ

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
አልለምደውም አልንቀውም
አልረሳውም አላቀለውም
አልለምደውም አልንቀውም
አልረሳውም አላቀለውም

ያንተ ሽታ ለሚጠፉት ነው የሞት መአዛ
ለሚድኑት ግን የህይወት እፎይታ
ለሚድኑት ግን የህይወት እፎይታ
ያንተ ሽታ ለሚጠፉት ነው የሞት መአዛ
ለሚድኑት ግን የህይወት እፎይታ
ለሚድኑት ግን የህይወት እፎይታ