From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ንጉሥ ፡ ስለወደደው ፡ እንዲህ ፡ ይደረግለታል
ንጉሥ ፡ ስላፈቀረው ፡ እንዲህ ፡ ይደረግለታል
ንጉሥ ፡ ስለወደደው ፡ ዘንጉ ፡ ይዘረጋለታል
ንጉሥ ፡ ስላፈቀረው ፡ ካባ ፡ ይደረብለታል (፪x)
እኔን ፡ ስለወደደኝ ፡ ኢየሱስን ፡ ሰጠኝ
እኔን ፡ ስላፈቀረኝ ፡ መድኃኒትን ፡ ሰጠኝ
እኔን ፡ ስለወደደኝ ፡ አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰጠኝ
እኔን ፡ ስላፈቀረኝ ፡ አማኑኤልን ፡ ሰጠኝ
ንጉሥ ፡ ስለወደደኝ ፡ እኔስ ፡ ዕድለኛ ፡ ነኝ
ንጉሥ ፡ ስላከበረኝ ፡ እኔስ ፡ ዕድለኛ ፡ ነኝ
ለእኔ ፡ የተደረገው ፡ ብዙ ፡ እኮ ፡ ነው
ለእኔ ፡ የተሰራው ፡ ብዙ ፡ እኮ ፡ ነው
አንድ ፡ በአንድ ፡ እቆጥራለሁ
የእርሱን ፡ መልካምነት ፡ እናገረዋለሁ (፪x)
ምን ፡ ያልተደረገ ፡ ያልሆነልኝ ፡ አለ
ከኢየሱስ ፡ ጀምሮ ፡ ለእኔ ፡ ያልተሰጠ
ከመልካምነቱ ፡ እኔን ፡ አጠገበ
ንጉሥ ፡ እኔን ፡ ወዶ ፡ እንዲህ ፡ አደረገ
ለእኔ ፡ የተደረገው ፡ ብዙ ፡ እኮ ፡ ነው
ለእኔ ፡ የተሰራው ፡ ብዙ ፡ እኮ ፡ ነው
አንድ ፡ በአንድ ፡ እቆጥራለሁ
የእርሱን ፡ መልካምነት ፡ እናገረዋለሁ (፪x)
አክሊል ፡ እንደለበሰ ፡ ያጌጠ ፡ ሙሽራ
ሕይወቴ ፡ በደሙ ፡ ታጥባ ፡ አምራ
በፊቱ ፡ የመግባትን ፡ ድፍረት ፡ አግኝታለች
ለልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ዛሬ ፡ ታዜምለታለች
ቸር ፡ ነው (፪x)
ምሕረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ፍቅሩ ፡ የማያልቅ ፡ ነው (፪x)
ወደደኝ ፡ አዳነኝ
ለክብሩ ፡ እኔን ፡ መረጠኝ (፪x)
(ወደደኝ ፡ አዳነኝ
ለክብሩ ፡ እኔን ፡ መረጠኝ (፪x))
|