From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ አጠገቤ ፡ ሆኗል ፡ ጌታ (፬x)
ከእንግዲህ ፡ የቱ ፡ ያስፈራኛል
እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል
ከእንግዲህ ፡ የቱ ፡ ያሰጋኛል
አባቴ ፡ ቅጥር ፡ ሆኖልኛል
በብቸኝነቴ ፡ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ማጣቴ
ትዝ ፡ ሲለኝ (፪x)
የለቅሶ ፡ እንጉርጉሮ ፡ ሲሰማ ፡ ከቤቴ
ትዝ ፡ ሲለኝ (፪x)
የእኔስ ፡ ነገር ፡ የእኔስ
በዓይን ፡ አይቶ ፡ ሳለቅስ
ያልራቀኝ ፡ ንጉሥ
የልጅነት ፡ ጓደኛ
ስሆን ፡ ያኔ ፡ ብቸኛ
ኢየሱስ ፡ አለኛ
አዝ፦ አጠገቤ ፡ ሆኗል ፡ ጌታ (፬x)
ከእንግዲህ ፡ የቱ ፡ ያስፈራኛል
እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል
ከእንግዲህ ፡ የቱ ፡ ያሰጋኛል
አባቴ ፡ ቅጥር ፡ ሆኖልኛል
የቅርብ ፡ ወንድሞቼ ፡ ሁሉ ፡ የከዱኝ
ትዝ ፡ ሲለኝ (፪x)
ያለርህራሄ ፡ ጉድጓድ ፡ የጣሉኝ
ትዝ ፡ ሲለኝ (፪x)
የእኔስ ፡ ነገር ፡ የእኔስ
በዓይን ፡ አይቶ ፡ ሳለቅስ
ያልራቀኝ ፡ ንጉሥ
የልጅነት ፡ ጓደኛ
ስሆን ፡ ያኔ ፡ ብቸኛ
ኢየሱስ ፡ አለኛ
አዝ፦ አጠገቤ ፡ ሆኗል ፡ ጌታ (፬x)
ከእንግዲህ ፡ የቱ ፡ ያስፈራኛል
እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል
ከእንግዲህ ፡ የቱ ፡ ያሰጋኛል
አባቴ ፡ ቅጥር ፡ ሆኖልኛል
ለእኔስ ፡ አይዞህ ፡ ብለው ፡ የሚያጽናኑኝ
ወዳጆቼም ፡ ችላ ፡ ቢሉኝ
የቅርቦቼም ፡ ችላ ፡ ቢሉኝ
እናት ፡ ልጇን ፡ እንኳን ፡ ብትረሳ
ልጄ ፡ ካለ ፡ የማይከዳ
ጌታ ፡ አለ ፡ ከእኔስ ፡ ጋራ (፪x)
|