From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እያስገረመኝ ፡ አሃሃሃ ፡ እያስደነቀኝ ፡ አሃሃሃ
የአንተ ፡ ምህረት ፡ አሃሃሃ ፡ ቃላት ፡ አሳጣኝ ፡ አሃሃሃ
መሽቶ ፡ እስኪነጋ ፡ አሃሃሃ ፡ መቁጠር ፡ እስከሚያቅት ፡ አሃሃሃ
የአንተን ፡ ደግነት ፡ አሃሃሃ ፡ እንከን ፡ የሌለበት ፡ አሃሃሃ
አዝ፦ ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ወዳጄ
ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ይኸውና ፡ በእጄ/ከእጄ
ከልቤ ፡ የፈለቀ ፡ የምሥጋና ፡ መስዋዕት
እሰዋልሃለሁ ፡ አሽተተው ፡ የእኔ ፡ አባት (፪x)
ተፈጸመ ፡ ብሎ ፡ ነግሮኛል ፡ ጌታዬ ፡ አሃሃሃ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ውሎ ፡ አሃሃሃ ፡ ተከፍሎ ፡ እዳዬ ፡ አሃሃሃ
እንዲህ ፡ እንዲያ ፡ እያለ ፡ ማነው ፡ የሚከሰኝ ፡ አሃሃሃ
ብሩክ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ አሃሃሃ ፡ ጠበቃ ፡ ስላለኝ ፡ አሃሃሃ
አዝ፦ ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ወዳጄ
ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ይኸውና ፡ በእጄ/ከእጄ
ከልቤ ፡ የፈለቀ ፡ የምሥጋና ፡ መስዋዕት
እሰዋልሃለሁ ፡ አሽተተው ፡ የእኔ ፡ አባት (፪x)
እስቲ ፡ ልነሳና ፡ አሃሃሃ ፡ ወደቤቴ ፡ ልውጣ ፡ አሃሃሃ
ለያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ አሃሃሃ ፡ መስዋዕቴን ፡ ልሰዋ ፡ አሃሃሃ
እንደ ፡ ስፍሪዳ ፡ አሃሃሃ ፡ ያማረ ፡ ምሥጋና ፡ አሃሃሃ
ላምጣ ፡ ልሰዋልህ ፡ አሃሃሃ ፡ ደግ ፡ አምላክ ፡ ነህና ፡ አሃሃሃ
አዝ፦ ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ወዳጄ
ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ይኸውና ፡ በእጄ/ከእጄ
ከልቤ ፡ የፈለቀ ፡ የምሥጋና ፡ መስዋዕት
እሰዋልሃለሁ ፡ አሽተተው ፡ የእኔ ፡ አባት (፪x)
|