የነፍሴ ፡ ማምለጫ (Yenefsie Mamlecha) - ኤፍሬም ፡ ዓለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዓለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 1.png


(1)

የነፍሴ ፡ ማምለጫ
(Yenefsie Mamlecha)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(3)

ጸሐፊ (Writer): ኤፍሬም ፡ አለሙ
(Ephrem Alemu
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዓለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

አንተ የኔ ጌታ የነፍሴ ማምለጫ
እታመንሃለው ሁሌ ጠዋት ማታ/2

አይቻለው ጌታ ክንድህን በህይወቴ
ስታድናት ያቺ ነፍሴን ከጠላቴ
እስከዛሬ የታደከኝ ለክብር ነው
ከዚ ሌላ ምን እላለው ተመስገን ነው

ተመስገን ነው ተባረክ ነው
ከፍ በል ነው ተወደስ ነው

ፀጋ የምትሰጥ የሰላም አለቃ
ሰላምን ሳገኝ ሙት መንፈሴ ነቃ
ገና አወራለው የእጆችህን ስራ
ብርሃን በውስጤ በእጥፍ ስለበራ

በእጥፍ ስለበራ ብርሃንህ ከኔ ጋራ/2
ጌታ ነህ ገናና ጌታ ባለዝና/2

አንተ የኔ ጌታ የነፍሴ ማምለጫ
እታመንሃለው ሁሌ ጠዋት ማታ/2

ቢታመኑህ ቢኮሩብህ ታኮራለህ
የመንግስትህ ወራሽ ዜጋ ታደርጋለህ
ከሚታየው ከሚሰማው ትለያለህ
ጌታ ቅዱስ ሰላሜ ነህ ትመቻለህ

ትመቻለህ/2 ትለያለህ/2

ፀጋ የምትሰጥ የሰላም አለቃ
ሰላምን ሳገኝ ሙት መንፈሴ ነቃ
ገና አወራለው የእጆችህን ስራ
ብርሃን በውስጤ በእጥፍ ስለበራ

በእጥፍ ስለበራ ብርሃንህ ከኔ ጋራ/2
ጌታ ነህ ገናና ጌታ ባለዝና/2

አንተ የኔ ጌታ የነፍሴ ማምለጫ
እታመንሃለው ሁሌ ጠዋት ማታ/2

አይቻለው ጌታ ክንድህን በህይወቴ
ስታድናት ያቺ ነፍሴን ከጠላቴ
እስከዛሬ የታደከኝ ለክብር ነው
ከዚ ሌላ ምን እላለው ተመስገን ነው

ተመስገን ነው ተባረክ ነው
ከፍ በል ነው ተወደስ ነው