የፍቅር ፡ አምላክ (Yefiqir Amlak) - ኤፍሬም ፡ ዓለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዓለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 1.png


(1)

የነፍሴ ፡ ማምለጫ
(Yenefsie Mamlecha)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(2)

ጸሐፊ (Writer): ኤፍሬም ፡ አለሙ
(Ephrem Alemu
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዓለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

አባብዬ ሳልውድህ ወደኸኝ ሳልመርጥህ መርጠኸኝ
በእየሱሴ የዘላለም ህይወት በነፃ ሰጠኸኝ

እድለኛ እድለኝ ነኝ/4

የፍቅር አምላክ የፍቅር ጌታ
ልጁን ገለጠው በኔ ሁኔታ
እሱን ለማምለክ ማንስ ተው ቢለኝ
የእየሱስ ፍቅር ውስጤ ገብቶብኝ

በዋጋ ገዝቶኛል ሃሌሉያ የራሴ አይደለሁም
እርሱም የኔ ሆኗል ማንም አይለየኝም
በእጆቹ መዳፍ ሃሌሉያ እየሱስ ቀርፆኛል
ታዲያ ከዚ ፍቅር ማንስ ይለየኛል

የፍቅር አይኑ አልተለየኝም
እባቡ ጊንጡ አልነደፈኝም
ይልቅ ከፍ ከፍ ከፍ አደረገኝ
በጠላቴ ፊት በዘይት ቀባኝ

የሰላሙ ንጉስ ሃሌሉያ በቤቴ ገባና ሃሌሉያ
በከፍታ አቆመኝ ዳግም ለምስጋና
የሚያስፈራኝ የለም ከእንግዲ በኋላ
ጌታ ጎኔ ቆሟል በፊቴም በኋላ

ምህረቱ ገኖ ባይኔ አይቻለው
እየሱስዬ እወደዋለው
አይረሳኝም የፍቅሩ ስራ
በቀራንዮ በዛ ተራራ

በመስቀል ላይ ሆኖ ሃሌሉያ ስለኔ አልቅሶ
አድኖኛል ጌታ እዳዬን ሰርዞ
በመስቀል ላይ ሆኖ ሃሌሉያ ስለኔ አልቅሶ
አድኖኛል ጌታ እዳዬን ሰርዞ