From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እታመነዋለው ታማኝ ስለሆነ
በቃሉ እውነተኛ ንጉስ የገነነ
የገነነ ጌታ የህይወቴ አለኝታ
ታሪክ ሰርቶ በእኔ ይገርመኛል መዳኔ
ገረመኝ መዳኔ ደነቀኝ መዳኔ
ኦ ገረመኝ መዳኔ ደነቀኝ መዳኔ
ጠላት የቆፈረው ጉድጓዶቼን ደፍኖ
እንዳልሞት አረገኝ ምህረቱን አግኖ
ዛሬ በነፃነት ይኸው ዘምራለው
ጠላት እየሰማ እየሱስ ጌታ ነው
አለልኝ ጌታ ጌታ የማይዝል የበረታ
አለልኝ ጌታ ጌታ ድለኛ ማይረታ
ይሸነፋል ብዬ እኔ ማልሰጋበት
እንዲያው ይባስ ብዬ ምወራረድበት
የገነነ ጌታ የህይወቴ አለኝታ
ታሪክ ሰርቶ በእኔ ይገርመኛል መዳኔ
ገረመኝ መዳኔ ደነቀኝ መዳኔ
ኦ ገረመኝ መዳኔ ደነቀኝ መዳኔ
ጠላት የቆፈረው ጉድጓዶቼን ደፍኖ
እንዳልሞት አረገኝ ምህረቱን አግኖ
ዛሬ በነፃነት ይኸው ዘምራለው
ጠላት እየሰማ እየሱስ ጌታ ነው
አለልኝ ጌታ ጌታ የማይዝል የበረታ
አለልኝ ጌታ ጌታ ድለኛ ማይረታ
ተደላድያለው በእርሱ ተማምኜ
እጅግ በሚመቸው ትከሻው ላይ ሆኜ
የሚገርመው ጌታ ሆኖልኛል መከታ
እኔ እንዳልሸነፍ ጠላቴን ድል መታ
ስይጣንን ድል መታ ጠላቴን ድል መታ
ጠላት የቆፈረው ጉድጓዶቼን ደፍኖ
እንዳልሞት አረገኝ ምህረቱን አግኖ
ዛሬ በነፃነት ይኸው ዘምራለው
ጠላት እየሰማ እየሱስ ጌታ ነው
አለልኝ ጌታ ጌታ የማይዝል የበረታ
አለልኝ ጌታ ጌታ ድለኛ ማይረታ
|