እኔ ፡ አልሰግድም (Enie Alsegdem) - ኤፍሬም ፡ ዓለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዓለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 1.png


(1)

የነፍሴ ፡ ማምለጫ
(Yenefsie Mamlecha)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2006)
ቁጥር (Track):

(8)

ጸሐፊ (Writer): ኤፍሬም ፡ አለሙ
(Ephrem Alemu
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዓለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

እኔ አልሰግድም ላቆምከው ምስል
አልዘምርም ለጠላት ክብር
ሰባት እጥፍ ቢነድ እሳቱ
ያድነኛል ዛሬም አቤቱ

ባያድነኝ እርሱ ይመለካል
የሲዖል ደጅ በእርሱ ተሰግቷል
የምድሩ ምን አስጨነቀኝ
የሰማዩ ከሰማረልኝ

የእየሱሴ ከሰመረ የእይሱሴ/2

ሃያል እግዚአብሔር ነው
በዘመናት ፀንቶ የቆመው
መንግስቱ ሁልግዜ ፅኑ
ድንቅን አርጓል በየዘመኑ

ጀግና እየሱስ ነው
እስካሁን ያልተበገረው
አዶናል አንደኛ ጌታ
በማንም የማይረታ

እዩት እንጂ ከትላንት ዛሬ
እዩት እንጂ ሲሰራ በኔ
መንፈስ ክብሩን እየጨመረ
በጠላት ሰፈር ጉድ እየሆነ
አንዱ ሲወጋ አንዱ ሲናጋ

በኔ ከበረ እየሱስ ጌታ
በኔ ተገልጧል እየሱስ ጌታ
በኔም ይሰራል እየሱስ ጌታ

እንደጎልያድ ለሚያስፈራራን
እኛ አንሰግድም ለሸለፈታም
እንዲት ጠጠር ለሱ ይበቃል
በግንባሩ ይፈነገላል

እኛ ብንደክም መቼ ይደክማል
አይታክትም ዛሬም ይሰራል
የዳዊትን ሰልፍ የተዋጋ
እየሱስ ነው የጌቶች ጌታ

እየሱስ ነው የጌቶቹ ሁሉ ጌታ/4

ሃያል እግዚአብሔር ነው ...
ጀግና እየሱስ ነው ...

ማዕበል ወጀብ ሁሉ ቢነሳ
አለ ጌታ ሁሌ እንዳንበሳ
መርከቢቷ ብትናወጥም
በእርሱ ጉልበት እኔ አልጠፋሁም

ሲገስፀው ሁሉ ተገዝቷል
ማዕበል ወጀብ ሁሉ ፀጥ ብሏል
የሁኔታ መቀያየሩ አያስፈራኝ ያ ውሽንፍሩ

አያስፈራኝ ማዕበል ወጀብ ውሽንፍሩ/4

ሃያል እግዚአብሔር ነው ...
ጀግና እየሱስ ነው ...

እዩት እንጂ ከትላንት ዛሬ
እዩት እንጂ ሲሰራ በኔ
መንፈስ ክብሩን እየጨመረ
በጠላት ሰፈር ጉድ እየሆነ
አንዱ ሲወጋ አንዱ ሲናጋ

በኔ ከበረ እየሱስ ጌታ
በኔ ተገልጧል እየሱስ ጌታ
በኔም ይሰራል እየሱስ ጌታ