የሚጤስ ፡ ጧፌን ፡ አላጠፋም (Yemitesewen Tuafien Alatefam) - ኤልያስ ፡ አብጤ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ኤልያስ ፡ አብጤ
(Elias Abte)

Lyrics.jpg


(1)

የሚጤስ ፡ ጧፌን ፡ አላጠፋም
(Yemitesewen Tuafien Alatefam)

ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤልያስ ፡ አብጤ ፡ አልበሞች
(Albums by Elias Abte)

የሚጤስ ፡ ጧፌን ፡ አላጠፋህም
ቅጥቅጥ ፡ ሸምበቆዬን ፡ ከቶ ፡ አልሰበርክም
ምሕረትህ ፡ በእኔ ፡ እጀጉን ፡ በዝቷል
የማዳን ፡ ክንድህን ፡ ዓይኔ ፡ አይቶታል

ክበር ፡ ተመስገን (፫) ዘላለም
 እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም(፪)

(፪x)
1)ቅጥቅጥ ሸንበቆን ጌታ የት ተሰብራለህ
የሚጠሰውንስም ጧፍ መች ታጠፋለህ
በሕይወት ታኖራለህ እንጂ ከቶ አትሰብርም
ይህ ነው ሥራህ ጌታ ክበር ለዘለዓለም

 እጅግ በደሌ በዝቶ የተዋረድኩ
 ዓይኔ ባንተ ተከፍቶ ጽድቅን አየሁ
 ሕይወትን ይዘህ ጌታ መጣህ ወደኔ
 ለነፍሴ ቤዛ ሆንክ ክበር መድሃኔ

አዝ

 2)እስከ ቀራንዮ ድረስ ጉድ ተሸክመህ
  ነብሴ በነብስህ ሲዋጅ ታሪክ ተፈፀመ
  የመዳኔ ምልክት ያኔ ታተመ
  የሰበረኝ ሀጥያቴ ጉልበቱ አከተመ

   ፍቅርህ እስከሞት ለኔ የበረታ ነው
   ከጥፋት ጉድጓድ ደርሶ ነብሴን አዳነው
   በኔ መቃብር ገብተህ ህይወት ሆነሀል
   የሚጤሰውን ጧፌን ጌታ አብርተሀል
  
 አዝ
   
 3)38 አመት እግሬን አጥቼ
  በቤተ ሳይዳ ደጃፍ በዋዛ ተኝቼ
  ሰው እንደማይቀርበኝም ባይንህ አየኸኝ
  እጆቼን ይዘህ ጌታ በእግሬ አቆምከኝ

   እንኳን አልጋ ልሸከም መሄድ የማልችል
   ፍፁም የተሳሰርኩኝ ሽባ ነበርኩኝ
   ታምራትህን በህይወቴ አሳየኸኝ
   ሌላ ምን እላለሁኝ ክበር ተመስገን

 አዝ

4)ወደ ባሪያህ ሕዝቂያስ ዓይንህን መልሰህ
በዕድሜው ላይ 15 ዓመት ጨምረህ
የፈሰሰውን ዕንባ ከዓይኖቹ አበስከው
በሕይወት እንዲኖር የሱስ ፈወስከው

 የሕዝቅያስስ ታሪክ የሕዝቅያስ ነው
 ለኔ ያደረክልኝ እጅግ ድንቅ ነው
 በነፍስም በስጋዬም ሙት የነበርኩኝ
 በቀራኒዮ ፍቅርህ በሕይወት ኑር አልከኝ