ዝም ፡ አልልም (Zem Alelem) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ደረጀ ፡ ከበደ
(Dereje Kebede)

Dereje Kebede 6.png


(6)

ዝም ፡ አልልም
(Zem Alelem)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:09
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Dereje Kebede)

ዝም አልልም አወራለሁ ታሪኩን
   ዘም አልልም እናገራለሁ ገድሉን
   ሞትን ትንሣኤውን ዳግመኛ ምጻቱን (*2)

ሰው ጎስቋላ ሆኖ ሃጢያቱ ውጦት
የእግዚአብሔር ልጅ ከላይ በሀዘን ተመልክቶት
ሊያድነዉ ወደደ ክብሩን ትቶ መቶ
ስጋ ለብሶ እንደሰው አሰው ማሕፀን ወቶ
    
   ዝም አልልም....(*2)

ጊዜው ደረሰና በግርግም ተወልዶ
አለምን ሊዋጃት ሆነ ምስኪን ባዶ
ሙታንን አስነሳ ለዲዳው አፍ ሰጠው
እውርን አበራ ለምፃሙን ዳሰሰው

    ዝም አልልም....(*2)

ሠው ግን አልፈቀደም አዳኙን ሊቀበል
ክፋቱ ገፋፋው ሊሰጠው ለመስቀል
በርባንም ተፈታ ኢየሱስ በግሩ ገባ
ስለ ሰው ሀጥያት የደም እንባ አነባ

    ዝም አልልም....(*2)

መቃብሩ ተናጋ ሳይቆይ በሰልስቱ
ከሙታን ተለየ እንደ አምላክነቱ
ሄደ ወደ አባቱ አረገ ወደላይ
እመጣለሁ ብሎ ሊፈርድ ባለም ላይ

    ዝም አልልም....(*2)