አምንሃለው (Amnihalehu) - ዳዊት ጌታቸው

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳዊት ጌታቸው
(Dawit Getachew)

Lyrics.jpg


(2)

አልበም
(Amnihalehu)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2021)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:14
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳዊት ጌታቸው ፡ አልበሞች
(Albums by Dawit Getachew)

ሁሉን ፡ የምትችል ፡ የአብርሃም ፡ አምላክ
ስለ ፡ ተስፋ ፡ ቃልህ ፡ ቅዱስ ፡ ስምህ ፡ ይባረክ
በእምነት ፡ በመጽናት ፡ ክብርህን ፡ ሰጥሃለው
አልጠራጠርም ፡ ቃልህን ፡ አምናለው

  አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ አምንሃለው
  ከማየው ፡ በላይ ፡ ቃልህን ፡ አምናለው
  በምንም ፡ አይነት ፡ እንደማተወኝ
  የከፈልክብኝ ፡ እየሱስ ፡ አሳየኝ
  እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ አምንሃለው
  ከራሴ ፡ በላይ ፡ ቃልህን ፡ አምናለው
  በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ እንደምትኖር ፡ ፀንትህ
  ለሚወዱህም ፡ ዋጋን ፡ እየሰጠህ

ከጠየኩህ ፡ እና ፡ ከማስበው ፡ በላይ
ማድረግ ፡ ለሚቻልህ ፡ ያለ ፡ አንዳች ፡ ከልካይ
ተስፋን ፡ በሚያስቆርጥ ፡ ባለቀ ፡ ነገር ፡ ላይ
ህይወት ፡ የምትዘራ ፡ አንተ ፡ አደለህም ፡ ወይ

  አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ አምንሃለው
  ከማየው ፡ በላይ ፡ ቃልህን ፡ አምናለው
  በምንም ፡ አይነት ፡ እንደማተወኝ
  የከፈልክብኝ ፡ እየሱስ ፡ አሳየኝ
  እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ አምንሃለው
  ከራሴ ፡ በላይ ፡ ቃልህን ፡ ይዣለው
  በዙፋንህ ፡ ላይ ፡ እንደምትኖር ፡ ፀንትህ
  ለሚወዱህም ፡ ዋጋን ፡ እየሰጠህ

በእምነት ፡ ጠብቃለው ፡ ቃልህን ፡ በተስፋ
የሚታይ ፡ ደመና ፡ ለጊዜው ፡ ቢጠፋ
ሃይሌ ፡ አንተ ፡ ነህና ፡ ፍጹም አልታክትም
በአንተ ፡ የታመኑትን ፡ ከቶ ፡ አትጥላችሀውም

ክንድህን ፡ ታምኜ ፡ ባንተ ፡ እመካለው
የነገርከኝን ፡ ተስፋ ፡ አደርጋለው
በቃልህ ፡ ታማኝ ፡ አምላክ ፡ ነህና
እጠብቅሃለው ፡ ሆኜ ፡ በምስጋና (፫X)