Daniel Amdemichael/Yesew Ej Yelielebet/Yesew Ej Yelielebet

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ርዕስ የሰው እጅ የሌለበት ዳንኤል አምደሚካኤል

አልበምየሰው እጅ የሌለበት

አዝ አዳነኝ በፀጋው አመሰግናለሁ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወቴ ጌታ ነው አምላክ በምህረቱ ባዘጋጀው መንገድ በወንጌሉ እምነት ሰጠኝ ዳግም ልደት በደስታ ከመዘመር ከማመስገን በቀር እኔማ ምን ልከፍል ከቶ ምን ልናገር የሰው እጅ የሌለበት የእኔ ብሎ የሚያኮራ በማመን የሚገኝ ጽድቅ የመስቀሉን ስራ

ፀጋው በእምነት ሆኖ አድኖኛል እግዚአብሔር በልጁ ሕይወትን ሰጥቶኛል ሁሉ ተፈጸመ በመስቀሉ በሰላም እንድኖር በዘለዓለም ፍቅሩ

ላመስግነው በዝማሬ ይኼን ታላቅ ጌታ ከጨለማ ለነጠቀኝ ከዚያ ክፉ ቦታ ለወደደኝ ብርሃኑን ላበራ በሕይወቴ መልካም ዜማ ለእርሱ ይሁን ይክበር መድሃኒቴ

አምላክ አበጃጀው ዘለዓለሜን አንድ ልጁን ሰጥቶ ክርስቶስ ብቃቴን የዘለላእም ህብረት ከአብ ጋራ አገኘሁ ልጅነት በክርስቶስ ስራ

ምሥጋናውን ልዘምረው ልናገር ወንጌሉን ጌታ ኢየሱስ እንደሚያድን ላብስር ምስራቹን የአምላክ ፍቃድ ኢኼ ሆኗል ሰዎን የሚያመልጡበት በልጁ ደም በእግዚአብሔር ጽድቅ አምነው ሚድኑበት አዝ አዳነኝ በፀጋው አመሰግናለሁ ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወ፡ ጌታ ነው አምላክ በምህረቱ ባዘጋጀው መንገድ በወንጌሉ እምነት ሰጠኝ ዳግም ልደት በደስታ ከመዘመር ከማመስገን በቀር እኔማ ምን ልከፍል ከቶ ምን ልናገር የሰው እጅ የሌለበት የእኔ ብሎ የሚያኮራ በማመን የሚገኝ ጽድቅ የመስቀሉን ስራ

ምሥጋና ለአምላክ ፍቅር ለታደገኝ እግሬን ከጨለማ መንገድ መለሰልኝ ብርሃንን አሳየኝ ቅዱስ ቃሉ ተፈጸመ እንዳለ ጌታ በመስቀሉ

ባመሰግን ይበዛል ወይ እኔስ በየእለቱ ቅኔ ብቀኝ ባሸበሸብ ብዘምር በቤቱ እልልስ ብል በታላቅ ድምጽ ብጮህ እስከደስታ ባጨበጭብ በመቅደሱ ለዚህ ክቡር ጌታ አዝ አዳነኝ በፀጋው አመሰግናለሁ ኢየሱስ ክስቶስ የሕይወቴ ጌታ ነው አምላክ በምህረቱ ባዘጋጀው መንገድ በወንጌሉ እምነት ሰጠኝ ዳግም ልደት በደስታ ከመዘመር ከማመስገን በቀር እኔማ ምን ልከፍል ከቶ ምን ልናገር የሰው እጅ የሌለበት የእኔ ብሎ የሚያኮራ በማመን የሚገኝ ጽድቅ የመስቀሉን ስራ

አሃ (፬x)