ልዘምር (Lezemer) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Lyrics.jpg


(7)

ልዘምር
(Lezemer)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፩ (2019)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

ልዘምር(፪) ፡

ልዘምር ልዘምር
ላዳነኝ ለእግዚአብሔር ልዘምር
ልቀኝለት ቅኔ
ታላቅ ሰሙ ይክበር መድኀኔ
ላምልከው ነፍሴን ታድጓታል
በሞቱ ሕይወትን ሰጥቷታል
ይህስ አይገርምም ወይ ታምር
ከሞት ያመለጠ ቆሞ ሲዘምር
 ታ ላ ቅ ነ ው ም ህ ረ ቱ
ልዘምር

አስደናቂ ፍቅር ከሰማይ የሆነ
ሰው ሆኖ ተወልዶ ሕይወቴን አዳነ
  አብ ሳበኝ በፍቅሩ ወልድ ቤዛ ለነፍሴ
   አተመኝ መንፈሱ አንድ አምላክ ሥላሴ
     
 ዘምር ዘምር አለኝ ጨምር እንደገና
ማዳኑ ተወርቶ ድንቁ መች ያልቅና
   ተዓምር ነው መዳኔ ምስጋና ለእግዚአብሔር
    የኢየሱስን ፍቅር ምህረቱን ልዘምር
     
ኢየሱስ ነው መንገዱ ካህን አስታራቂ
በደሌን ይቅር ባይ የነፍሴ ጠባቂ
  በመንፈስ ላምልከዉ ለአብ ይሁን ስግደት
   እግዚአብሔር የሚወደዉ አይጓደልበት