From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ አንበሳ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ነው
ንጉሥ ፡ ነው ፡ የጌቶችም ፡ ጌታ ፡ ነው
ሁሉንም ፡ አሸንፏል ፡ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሏል
ኧረ ፡ ማነው ፡ የሚመስለው
የእኛ ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)
የታረደው ፡ በግ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ምሥጋናም ፡ ክብርም ፡ የተገባው ፡ ነው
ጥበብም ፡ ውዳሴም ፡ ለእርሱ ፡ ነው
ድል ፡ አድራጊ ፡ ጌታ ፡ ነው
አዝ፦ አንበሳ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ነው
ንጉሥ ፡ ነው ፡ የጌቶችም ፡ ጌታ ፡ ነው
ሁሉንም ፡ አሸንፏል ፡ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሏል
ኧረ ፡ ማነው ፡ የሚመስለው
የእኛ ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)
ሃያ ፡ አራቱ ፡ ሽማግሌዎች
ወድቀው ፡ በፊቱ ፡ የሚሰግዱለት
ዘለዓለም ፡ ሊነግሥ ፡ ይገባዋል
ኢየሱስ ፡ ሁሉን ፡ ረቷል
አዝ፦ አንበሳ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ነው
ንጉሥ ፡ ነው ፡ የጌቶችም ፡ ጌታ ፡ ነው
ሁሉንም ፡ አሸንፏል ፡ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሏል
ኧረ ፡ ማነው ፡ የሚመስለው
የእኛ ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)
በአምባ ፡ ላይ ፡ ፈረስ ፡ የተቀመጠው
እውነተኛና ፡ ታማኝ ፡ የሆነው
በትክክል፡ ይፈርዳል ፡ ይዋጋል
ጌታን ፡ ማን ፡ ይችለዋል?!
አዝ፦ አንበሳ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ነው
ንጉሥ ፡ ነው ፡ የጌቶችም ፡ ጌታ ፡ ነው
ሁሉንም ፡ አሸንፏል ፡ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሏል
ኧረ ፡ ማነው ፡ የሚመስለው
የእኛ ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)
ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ ማንም ፡ አያውቀው
ከሥሞች ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ሥም ፡ አለው
ኢየሱስ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ነው
የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ ነው
አዝ፦ አንበሳ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ነው
ንጉሥ ፡ ነው ፡ የጌቶችም ፡ ጌታ ፡ ነው
ሁሉንም ፡ አሸንፏል ፡ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሏል
ኧረ ፡ ማነው ፡ የሚመስለው
የእኛ ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)
|