Dagmawi Tilahun/Feqer Yeqer Yalew/Feqer Yeqer Yalew

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኧረ እኔ ማነኝ ቤቴስ ምንድነው ከጣሪያዬ በታች ኢየሱስየገባው (፪x) ምህረት የበዛለት ፍቅር ይቅር ያለው ደግሞ ያየ ቸርነቱን እንደ እኔ ያለ ማነው (፪x)

(እኔማ) ሞተ ስባል ያለሁ (እኔማ) ጠፋ ስባል የቆምኩ (እኔማ) ምንም እንዳላየ (እኔማ) እንዴት ዝም እላለሁ (እኔማ) እኔማ ስላንተ (እኔማ) ለሃገር ለምድሩ (እኔማ) አልጠግብ አውርቼ (እኔማ) ምህረት አግኝቼ

ምህረት የበዛለት ፍቅር ይቅር ያለው ደግሞ ያየ ቸርነቱን እንደኔ ያለ ማነው (፪x)

(እኔማ) ያንን ዘመን ሳስብ (እኔማ) እንባ ይቀድመኛል (እኔማ) ሞት ሽረት ሆኖብኝ (እኔማ) ማን አለሁ ብሎኛል (እኔማ) ከበለሱም በታች (እኔማ) ድምጽህን መስማቴ (እኔማ) ያ ነው ሰው ያረገኝ (እኔማ) የመኖር ምክንያቴ

ኧረ እኔ ማነኝ ቤቴስ ምንድነው ከጣሪያዬ በታች ኢየሱስ የገባው (፪x)