ኢየሱስ (Iyesus) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Caleb Tesfaye 6.jpg


(6)

አልበም
(Tensae Ale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

በምድር ላይ የገነኑ
ሞት ሲመጣ ሲፈተኑ
ሊያመልጡ አልቻሉም በቃቸው
ስጋ ለባሽ አፈር ናቸው

ግን ይሄ ንጉስ መቃብሩን
ተሰማለት መፈንቀሉን
ወጣ የሙታኑ በኩር
የክቡራን ሁሉ ክቡር

እየሱስ ጌታ ነው
እየሱስ ህያው ነው
እየሱስ ጀግና ነው
እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ

ስሙ ሲጠራ የማይፈራ
"እኔ ነኝ" ያለ ተራራ
ይናዳል ይሆናል ሜዳ
ታይቷል ስንቱን ሰው ሲረዳ

ወጀቡም ፀጥ ማዕበልም ፀጥ
ካዘዘ እሱ ማን ሊቀመጥ
ግርማው ክብሩ የተለየ
ገናና ከፍ ብሎ የቆየ

እየሱስ ሁሉን ቻይ ነው
እየሱስ ሃያል ነው
እየሱስ ብርቱ ነው
እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ

ነፍስ ያስጨነቁ አጋንንቶች
ከንቱ ምናምንቴዎች
ሲታዘዙ ወዮ እያሉ
በእሳት ተገርፈው ይለቃሉ

ማን ሰማና ማን አየና?
ይህን የመሰለ ጀግና
ሰማይ ቢወጣ ምድር ላይ
አይን እሱን የመሰለ አያይ

እየሱስ ገናና ነው
እየሱስ ልዩ ነው
እየሱስ ታላቅ ነው
እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ

ለጥያቄ ሁሉ መልሱ
ለበሽታ ሁሉ ፈውሱ
አንድ እና አንድ እሱ ብቻ
ቁልፍ ነው የሁሉ መፍቻ

ደቆሮውን፣ ዲዳውን
መሄድ ያልቻለ ሽባውን
ኧረ ስንቱን ነፃ አወጣ
ቤቱ ድረስ እየመጣ

እየሱስ ፈዋሽ ነው
እየሱስ ተስፋ ነው
እየሱስ አዳኝ ነው
እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ