From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ:- ተገልብጧል ፡ ታሪክ ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ ተፈጥሯል
ንጉሡ ፡ እግዚአብሔር ፡ ምስኪኑን ፡ እረድቶታል
ተዓምር ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ቆመ ፡ በእግሩ
ተወራ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ በአምላኩ ፡ እርሱ ፡ መክበሩ (፪x)
ይሄው ፡ ተራ ፡ ደርሶት ፡ ምሥጋናን ፡ ሊሰዋለት
ወጣ ፡ አደባባይ ፡ ላይ ፡ ማቁ ፡ ተቀዳዶለት
አከናውኖለታል ፡ ደስታው ፡ ወሰን ፡ ልክ ፡ የለው
ይሄን ፡ ችግረኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አሰበው
አዝ:- ተገልብጧል ፡ ታሪክ ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ ተፈጥሯል
ንጉሡ ፡ እግዚአብሔር ፡ ምስኪኑን ፡ እረድቶታል
ተዓምር ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ቆመ ፡ በእግሩ
ተወራ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ በአምላኩ ፡ እርሱ ፡ መክበሩ (፪x)
ተባርኮለት ፡ ጓዳው ፡ መከራውን ፡ እረሳው
ታምኖበታልና ፡ ጌታው ፡ በብዙ ፡ እረዳው
ምርኮው ፡ ተመለሰ ፡ የአጥፍ ፡ እጥፍ ፡ ሆነለት
ካሰው ፡ ያጣውን ፡ ሁሉ ፡ እየነዳ ፡ አመጣለት
አዝ:- ተገልብጧል ፡ ታሪክ ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ ተፈጥሯል
ንጉሡ ፡ እግዚአብሔር ፡ ምስኪኑን ፡ እረድቶታል
ተዓምር ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ቆመ ፡ በእግሩ
ተወራ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ በአምላኩ ፡ እርሱ ፡ መክበሩ (፪x)
ተራራ ፡ ላይ ፡ አወጣው ፡ የናቁት ፡ ሁሉ ፡ እንዲያዩት
በምላስ ፡ አለንጋ ፡ ሌት ፡ ተቀን ፡ የገረፉት
ሲሸላልመው ፡ አዪ ፡ በሞገስ ፡ ሲቀባባው
ውስጡንም ፡ ላዩንም ፡ እንደ ፡ አበባ ፡ ሲያፈካው
አዝ:- ተገልብጧል ፡ ታሪክ ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ ተፈጥሯል
ንጉሡ ፡ እግዚአብሔር ፡ ምስኪኑን ፡ እረድቶታል
ተዓምር ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ቆመ ፡ በእግሩ
ተወራ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ በአምላኩ ፡ እርሱ ፡ መክበሩ (፪x)
ቀና ፡ አለ ፡ ከአንገቱ ፡ ማቀርቀሩ ፡ ቀረና
ያስተከዘው ፡ ኑሮ ፡ ድንገት ፡ ተቀየረና
እነዛም ፡ ዘባቾች ፡ ሲረቱ ፡ አሉ ፡ ተደንቀው
የረዳህን ፡ አምላክ ፡ እርሱን ፡ ነው ፡ የምናመልከው
አዝ:- ተገልብጧል ፡ ታሪክ ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ ተፈጥሯል
ንጉሡ ፡ እግዚአብሔር ፡ ምስኪኑን ፡ እረድቶታል
ተዓምር ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ቆመ ፡ በእግሩ
ተወራ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ በአምላኩ ፡ እርሱ ፡ መክበሩ (፪x)
ተአምር ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ሰው ፡ ቆመ ፡ በእግሩ
ተወራ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ በአምላኩ ፡ እርሱ ፡ መክበሩ (፫x)
|