ብዙ ፡ ትቶልኛል (Bezu Tetolegnal) - ብዙ ፡ ሙሉጌታ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ብዙ ፡ ሙሉጌታ
(Bezu Mulugeta)

Bezu Mulugeta Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አልበም
(፩)

ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ አልበሞች
(Albums by Bezu Mulugeta)

አዝ፦ ብዙ ፡ ትቶልኛል ፡ ብዙ ፡ እወደዋለሁ
ብዙ ፡ እኔን ፡ ምሮኛል ፡ ብዙ ፡ አከብረዋለሁ
በብዙ ፡ ምሥጋና ፡ ፊቱ ፡ እቀርባለሁ
በብዙ ፡ ዝማሬ ፡ ጌታን ፡ አከብራለሁ

ገበናን ፡ ሰው ፡ መግለጥ ፡ ይወዳል
ኃጢአትን ፡ መቼ ፡ ይቅር ፡ ይላል
የእኔ ፡ ውድ ፡ ከዝህ ፡ ሁሉ ፡ ልዩ ፡ (፪×)
ችሎኛል ፡ ሰዎች ፡ ይህንን ፡ ስሙኙ ፡ (፪×)

አዝ

ስንቆም ፡ ሞገስ ፡ የሚያለብሰን
ጻድቃኖች ፡ አድርጐ ፡ የቆጠረን
ኢየሱስ ፡ ብዙ ፡ ትቶልናል ፡ (፪×)
ምሕረት ፡ ዛሬም ፡ ያኖረናል ፡ (፪×)

አዝ

ለመውገር ፡ ሁሉም ፡ ይቸኩላል
ድንጋዩን ፡ በእጁ ፡ ተሸሟል
ኢየሱስ ፡ የሰውን ፡ ድካም ፡ ያውቃል ፡ (፪×)
ከአመድ ፡ ላይ ፡ ምስኪኑን ፡ ያነሳል ፡ (፪×)

አዝ

ውለታው ፡ ለእኔ ፡ በዝቶብኛል
ነውሬን ፡ ኢየሱስ ፡ ወስዶልኛል
ውበቴ ፡ ድምቀቴ ፡ ሽቶዬ ፡ (፪×)
ጠረኔ ፡ ሆነልኝ ፡ ጌታዬ ፡ (፪×)

አዝ

ብዙ ፡ ትቶልኛል ፡ ብዙ ፡ እወደዋለሁ
ብዙ ፡ እኔን ፡ ምሮኛል ፡ ብዙ ፡ አከብረዋለሁ
በብዙ ፡ ምሥጋና ፡ ፊቱ ፡ እቀርባለሁ ፡ (፬×)
በብዙ ፡ ዝማሬ ፡ ጌታን ፡ አከብራለሁ ፡ (፬×)


https://www.youtube.com/watch?v=qgHR72jvFhs&list=RDqgHR72jvFhs&start_radio=1