Bethlehem Wolde/tichewalew/tichewalew

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ቤቴልሔም ወልዴ

አዝ
ትቼዋለሁ ሃሳቤን ባንተ ላይ ጥላለሁ
ትቼዋለሁ ጭንቀቴን ባንተ ላይ ጥላለሁ
ምታስብልኝ አምላኬ በሰማይ አለልኝ
ምታስብልኝ ጌታዬ በሰማይ አለልኝ። (2×)

ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል
የኛ ጭንቀት ምን ይረባናል
እርሱ ስለኛ ያስባልና
ሃሳብን በርሱ ላይ እንጣል። (2×)
አዝ

የሰማዩ ወፎች ከቶ አይዙሩም
አጭደው በጎተራ አይጨምሩም
የሰማዩ ጌታ ይመግባቸዋል
ከእነርሱ ይበልጥ ይወደናል። (2×)
አዝ

አንተ ስለ እኔ ከላይ ወርደሃል
ነፍሰህን ስለ እኔ ሰጥተሃል
ያስጨነቀኝን ጠላት ጥለህልኛል
ልቤንም በሰላም ሞልተሃል። (2×)
አዝ