From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ቤተልሔም ፡ ወልዴ (Bethlehem Wolde)
|
|
|
|
(Volume)
|
እረኛዬ (Eregnaye)
|
| ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፰ (2016)
|
| ቁጥር (Track):
|
፪ (2)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
|
የቤተልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች (Albums by Bethlehem Wolde)
|
|
|
ትቼዋለሁ ሃሳቤን ባንተ ላይ እጥላለሁ
ትቼዋለሁ ጭንቀቴን ባንተ ላይ እጥላለሁ
ምታስብልኝ አምላኬ በሰማይ አለህልኝ
ምታስብልኝ ጌታዬ በሰማይ አለህልኝ (2X)
ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል
የእኛ ጭንቀት ምን ይረባናል?
እሱ ስለ እኛ ያስባልና
ሃሳብን በሱ ላይ እንጣል
ትቼዋለሁ ሃሳቤን ባንተ ላይ እጥላለሁ
ትቼዋለሁ ጭንቀቴን ባንተ ላይ እጥላለሁ
ምታስብልኝ አምላኬ በሰማይ አለህልኝ
ምታስብልኝ ጌታዬ በሰማይ አለህልኝ
የሰማይ ወፎች ከቶ አይዘሩም
አጭደው በጎተራ አይከምሩም
የሰማይ ጌታ ይመግባቸዋል
ከነሱ ይበልጥ ይወደናል
ትቼዋለሁ ሃሳቤን ባንተ ላይ እጥላለሁ
ትቼዋለሁ ጭንቀቴን ባንተ ላይ እጥላለሁ
ምታስብልኝ አምላኬ በሰማይ አለህልኝ
ምታስብልኝ ጌታዬ በሰማይ አለህልኝ
አንተ አስበህልኝ ከላይ ወርዳሃል
ነፍስህን ስለኔ ሰጥተሀል
ያስጨነቀኝ ጠላት ጥለህልኛል
ልቤንም በሰላም ሞልተሀል
ትቼዋለሁ ሃሳቤን ባንተ ላይ እጥላለሁ
ትቼዋለሁ ጭንቀቴን ባንተ ላይ እጥላለሁ
ምታስብልኝ አምላኬ በሰማይ አለህልኝ
ምታስብልኝ ጌታዬ በሰማይ አለህልኝ
|