From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አቤት ፡ አምላኬ ፡ ያደገልኝን ፡ ሳስተውለው ፡ ባረኩህ (፪x)
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ያደረክልኝ ፡ ሳስተውሰው ፡ ወደድኩህ (፪x)
ለካስ ፡ እንዲህ ፡ ነው (፫x)
ነፍሴን ፡ ያዳንካት ፡ ከጉድ ፡ ነው
ለካስ ፡ እንዲህ ፡ ነው (፫x)
ነፍሴን ፡ ያዳንካት ፡ ከሞት ፡ ነው (፪x)
የዘለዓለም ፡ ፍቅር ፡ የዘላለም ፡ ሕይወት
ይሄው ፡ አሰጥቶኛል ፡ ወደ ፡ አብ ፡ መግባት
ኢየሱስ ፡ አየሁት ፡ የፍቅርህን ፡ ልኩን
አኔ ፡ አስገዝቶኛል ፡ እስከ ፡ ሞት ፡ መሆኑ
ማንም ፡ ባያውቅህ ፡ የታወቅህ ፡ ነህ
ማንም ፡ ባያምንህ ፡ የታመንህ ፡ ነህ
እኔስ ፡ አውቄህ ፡ ሆንኩኝ ፡ ምስክር
ሳላመነታ ፡ ሳልደናገር (፪x)
እኔስ ፡ አውቄ ፡ ሆንኩኝ ፡ ምስክር
ሳላመነታ ፡ ሳልጠራጠር
ታሪክ ፡ ተረድቼ ፡ አይደለም ፡ ሲነገር ፡ ሰምቼ ፡ ብቻ ፡ አይደለም
የሰራህልኝን ፡ አስቤ ፡ እከተልሃለሁ ፡ ከልቤ
ታሪክ ፡ ተረድቼ ፡ አይደለም ፡ ሲነገር ፡ ሰምቼ ፡ ብቻ ፡ አይደለም
ያደረክልኝን ፡ አስቤ ፡ እኖርልሃለሁ ፡ ከልቤ
አውቄያለሁ ፡ አውቄያለሁ ፡ ተረድቻለሁ
የመኖሬ ፡ ትርጉም ፡ ሆኖ ፡ አግኝቼዋለሁ (፪x)
አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ ለኔ ፡ ማነው
ማንስ ፡ ነው ፡ ልሙትልሽ ፡ ያለው
ከሰማያት ፡ ወርደህ ፡ ያዳንከኝ ፡ አንተ
ለዘለዓለም ፡ ልገዛልህ ፡ ላንተ
ከሰማያት ፡ ወርደህ ፡ አድነህኛል
የሰራህልኝን ፡ ልቤ ፡ አውቆታል
ሳመልክህ ፡ በደስታ ፡ ሳከብርህ ፡ በደስታ
ለነፍሴ ፡ በሞት ፡ ፈንታ ፡ መዳን ፡ አውጀሃልና (፪x)
እንግዲህ ፡ ነፍሴን ፡ ካዳንክልኝማ
በደስታ ፡ እኖራለሁ ፡ በደስታ ፡ ላንተ ፡ ጌታ
በደስታ ፡ እኖራለሁ ፡ በደስታ
እንግዲህ ፡ ነፍሴን ፡ ካዳንክልኝማ
በውዴታ ፡ እገዛለሁ ፡ በውዴታ ፡ ላንተ ፡ ጌታ
በውዴታ ፡ እገዛለሁ ፡ በውዴታ
|