መሪዬ ፡ ነህ (Meriyie Neh) - ቤተልሔም ፡ ቦጋለ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቤተልሔም ፡ ቦጋለ
(Bethlehem Bogale)

Lyrics.jpg


(1)

መሪዬ ፡ ነህ
(Meriyie Neh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ቦጋለ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Bogale)

በምድረበዳው(፪)
ጥሎ ፡ የማይሄድ ፡ ጌታ ፡ የሚያሳርፍ ፡ ነው
ከእናቴ ፡ ማህጸን ፡ ስላወቀኝ ፡ ጌታ
እንዳልጠፋ ፡ እንዳልሞት ፡ በብዙ ፡ ጥበቃ
እየጠበቀኝ ፡ እየደገፈኝ
እረኛዬ ፡ ሆኖ ፡ ጌታ ፡ አሳደገኝ

መሪዬ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ብልህ ፡ ምን ፡ ያንስሃል ፡ ኢየሱሴ
ውበት ፡ ደምግባቴ ፡ ብልህ ፡ ምን ፡ ያንስሃል ፡ ኢየሱሴ(፪)

በመከራዬ ፡ ላይ ፡ ጋሻ ፡ የሆነኝ
ተስፋ ፡ በሌለበት ፡ ፍቅሩ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እጄን ፡ የያዘኝ
ከማንም ፡ አብልጦ ፡ እኔን ፡ ሚጠጋጋ
(ኢየሱስ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ዋስ ፡ ጠበቃ)፪

የገረመኝ(፫) ፡ የጌታ ፡ ማዳን ፡ ለእኔ ፡ ገብቶኝ
የደነቀኝ(፪) ፡ የጌታ ፡ ፍቅር ፡ ለእኔ ፡ ገብቶኝ
እናገራለሁ ፡ አፌን ፡ ሞልቼ
??? ፡ በሮቼን

በምሥጋና(፫) ፡ ስሙን ፡ ላክብር ፡ እንደገና
በዕልልታ(፫) ፡ ዛሬም ፡ አለሁ ፡ በከፍታ

ክብሩን ፡ ትቶ ፡ ለእኔ ፡ ከሰማይ ፡ መጣልኝ
እዳዬን ፡ ከፈለ ፡ ከሲዖል ፡ አወጣኝ
ምን ፡ ልበል ፡ እንግዲህ ፡ ቃላቶች ፡ የሉኝም
የፍቅሩን ፡ ጥልቀት ፡ መግለጽ ፡ አልቻልኩኝም

የገረመኝ(፫) ፡ የጌታ ፡ ማዳን ፡ ለእኔ ፡ ገብቶኝ
የደነቀኝ(፪) ፡ የጌታ ፡ ፍቅር ፡ ለእኔ ፡ ገብቶኝ
እናገራለሁ ፡ አፌን ፡ ሞልቼ
??? ፡ በሮቼን

በምሥጋና(፫) ፡ ስሙን ፡ ላክብር ፡ እንደገና
በዕልልታ(፫) ፡ ዛሬም ፡ አለሁ ፡ በከፍታ

ማቄ ፡ ተቀደደ ፡ ዳግም ፡ ተወለድኩኝ
ልጅ ፡ የምሆንለት ፡ አባት ፡ አገኘሁኝ
ይኸው ፡ በተራዬ ፡ እመሰክራለሁ
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ብዬ ፡ አወራለሁ

የገረመኝ(፫) ፡ የጌታ ፡ ማዳን ፡ ለእኔ ፡ ገብቶኝ
የደነቀኝ(፪) ፡ የጌታ ፡ ፍቅር ፡ ለእኔ ፡ ገብቶኝ
እናገራለሁ ፡ አፌን ፡ ሞልቼ
??? ፡ በሮቼን

በምሥጋና(፫) ፡ ስሙን ፡ ላክብር ፡ እንደገና
በዕልልታ(፫) ፡ ዛሬም ፡ አለሁ ፡ በከፍታ

በምድረበዳው(፪)
ጥሎ ፡ የማይሄድ ፡ ጌታ ፡ የሚያሳርፍ ፡ ነው
ከእናቴ ፡ ማህጸን ፡ ስላወቀኝ ፡ ጌታ
እንዳልጠፋ ፡ እንዳልሞት ፡ በብዙ ፡ ጥበቃ
እየጠበቀኝ ፡ እየደገፈኝ
እረኛዬ ፡ ሆኖ ፡ ጌታ ፡ አሳደገኝ

መሪዬ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ብልህ ፡ ምን ፡ ያንስሃል ፡ ኢየሱሴ
ውበት ፡ ደምግባቴ ፡ ብልህ ፡ ምን ፡ ያንስሃል ፡ ኢየሱሴ(፪)