From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ከተሸሸኩበት ፡ መንደሬ
መጣ ፡ ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ ሰፈሬ
ጠራኝ ፡ ቀርቦ ፡ በቁልምጫው
ሊያስገባኝ ፡ ወደ ፡ ጉያው
የወዳጄ ፡ የአምላኬ
ጥሪው ፡ ደርሶኛል
ምን ፡ አደርጋለሁ
ቀሪው ፡ ዘመኔን ፡ ሰጥቼዋለሁ
ይስራበት ፡ ይክበርበት
ያለው ፡ አላማ ፡ ፈቃድ ፡ ሀሳቡ
ይጠቅለል ፡ በእኔ ፡ ይድረስ ፡ ከግቡ
ሲጠራኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ)
ሲለየኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ)
ሲቀባኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ)
ሲመርጠኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) (፪x)
መገለጫው ፡ ነው ፡ መገለጫው
ለሰማይ ፡ ወኪል ፡ የምድር ፡ ጨው
የምድርን ፡ ክፋት
መርገም ፡ ሰባሪ
የሰላም ፡ ዘማች ፡ ለሰማይ ፡ ጥሪ (፪x)
ሲጠራኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ)
ሲለየኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ)
ሲቀባኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ)
ሲመርጠኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ (፪x)
ማያንገራግረው ፡ ማያመቻምቸው
ትዳር ፡ ባለበት ፡ ሰፈር
ራሱን ፡ የማይጠምደው
ጠሪውን ፡ ሲያስደስተው
ሲገኝ ፡ በጸና ፡ እምነቱ
ማረጉ ፡ ነው ፡ በላዩ
ሚታየው ፡ ሽልማቱ (፪x)
ወዶ ፡ ዘማች ፡ ወዶ ፡ ዘማች
ለወንጌሉ ፡ ወዶ ፡ ዘማች
ፈቅዶ ፡ ዘማች ፡ ፈቅዶ ፡ ዘማች
ለዚህ ፡ ጥሪ ፡ ፈቅዶ ፡ ዘማች
ማነው (ወዶ ፡ ዘማች)
ማነው (ለዚህ ፡ ጥሪ)
ማነው (ራሱን ፡ ሰቶ)
ማነው (ጌታውን ፡ አስጠሪ)
ማነው (እኔ ፡ ነኝ)
ማነው (እኔ ፡ ነኝ)
ማነው (እኔ ፡ ነኛ)
ማነው (ለወንጌሉ)
ማነው (ዘማች ፡ አርበኛ)
ማነው (፬x)
ማነው
|