From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
አዜብ ፡ ኃይሉ (Azeb Hailu)
|
|
|
|
፭ (5)
|
አልበም (፭)
|
| ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፱ (2017)
|
| ቁጥር (Track):
|
፲ (10)
|
| ርዝመት (Len.):
|
4:23
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
|
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች (Albums by Azeb Hailu)
|
|
|
ወደ ፡ አምላኬ ፡ ቤት ፡ ወደ ፡ ማደሪያው
አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ይዤ ፡ የምገባው
ወደ ፡ አምላኬ ፡ ቤት ፡ ወደ ፡ መቅደሱ
አለኝ ፡ አምልኮ ፡ የሚሆን ፡ ለእርሱ
ወደ ፡ አምላኬ ፡ ቤት ፡ ወደ ፡ ማደሪያው
አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ይዤ ፡ የምገባው
ወደ ፡ አምላኬ ፡ ቤት ፡ ወደ ፡ መቅደሱ
አለኝ ፡ አምልኮ ፡ የሚሆን ፡ ለእርሱ
በአደባባዩ ፡ በቤቱ ፡ ደጅ
ምሥጋናው ፡ ይታወጅ
በክብር ፡ ቤቱ ፡ ዙፋኑ ፡ ዙሪያ
ይዘመር ፡ ሃሌሉያ
በልቤ ፡ ሞልቶ ፡ የተረፈው
የምሥጋን ፡ ቃል ፡ ዝማሬ ፡ ነው
መክፈል ፡ ባልችልም ፡ የእርሱን ፡ ውለታ
ፊቱ ፡ ቀርቤ ፡ ላሰማ ፡ ዕልልታ
ላደረገልኝ ፡ ለሰራው ፡ ሁሉ
ወዳጅ ፡ ዘመዴ ፡ ክበር ፡ ይበሉ
በጸሎት ፡ ምልጃ ፡ ለቃተታችሁ
ዛሬ ፡ ምሥጋና፡ ቀን ፡ ነው ፡ አይዟችሁ
ወደ ፡ አምላኬ ፡ ቤት ፡ ወደ ፡ ማደሪያው
አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ይዤ ፡ የምገባው
ወደ ፡ አምላኬ ፡ ቤት ፡ ወደ ፡ መቅደሱ
አለኝ ፡ አምልኮ ፡ የሚሆን ፡ ለእርሱ
ወደ ፡ አምላኬ ፡ ቤት ፡ ወደ ፡ ማደሪያው
አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ይዤ ፡ የምገባው
ወደ ፡ አምላኬ ፡ ቤት ፡ ወደ ፡ መቅደሱ
አለኝ ፡ አምልኮ ፡ የሚሆን ፡ ለእርሱ
በአደባባዩ ፡ በቤቱ ፡ ደጅ
ምሥጋናው ፡ ይታወጅ
በክብር ፡ ቤቱ ፡ ዙፋኑ ፡ ዙሪያ
ይዘመር ፡ ሃሌሉያ
ስለቴን ፡ ልክፈል ፡ ቃል ፡ ኪዳኔን
ለክብርህ ፡ ቢሆን ፡ ብዬ ፡ ያልኩትን
ባይመጣጠን ፡ ከአንተ ፡ ውለታ
ግን ፡ ዝም ፡ አልልም ፡ ልሰዋው ፡ ላምጣ
ጣልቃ ፡ እየገባ ፡ በሕይወት ፡ መንገዴ
የመራኝ ፡ እጅህ ፡ ክንድህ ፡ አይደል ፡ እንዴ
ታዲያ ፡ ስለምን ፡ ዕልልታን ፡ ልርሳ
ይልቅ ፡ ልጨምር ፡ ላብዛ ፡ ሙገሳ ፡
ወደ ፡ አምላኬ ፡ ቤት ፡ ወደ ፡ ማደሪያው
አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ይዤ ፡ የምገባው
ወደ ፡ አምላኬ ፡ ቤት ፡ ወደ ፡ መቅደሱ
አለኝ ፡ አምልኮ ፡ የሚሆን ፡ ለእርሱ
ወደ ፡ አምላኬ ፡ ቤት ፡ ወደ ፡ ማደሪያው
አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ይዤ ፡ የምገባው
ወደ ፡ አምላኬ ፡ ቤት ፡ ወደ ፡ መቅደሱ
አለኝ ፡ አምልኮ ፡ የሚሆን ፡ ለእርሱ
በአደባባዩ ፡ በቤቱ ፡ ደጅ
ምሥጋናው ፡ ይታወጅ
በክብር ፡ ቤቱ ፡ ዙፋኑ ፡ ዙሪያ
ይዘመር ፡ ሃሌሉያ
|