From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ነፍሴ ፡ በአንተ ፡ ሐሴት ፡ ታደርጋለች X፬
እግዚአብሔር ፡ የእኔ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ እያለች X፬
ዝማሬዋ ፡ ኃይሏ ፡ ጉልበት ፡ ሆነህላት
ያለፈውን ፡ ዘመን ፡ ክንድህ ፡ አሻገራት
አንተ ፡ ዘንድ ፡ እጅጉን ፡ ብዙ ፡ ኃይል ፡ አለና
እስከፍጻሜውም ፡ በቤትህ ፡ ሚያጸና
ነፍሴ ፡ በአንተ ፡ ሐሴት ፡ ታደርጋለች X፬
እግዚአብሔር ፡ የእኔ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ እያለች X፬
የእኔ ፡ የእኔ ፡ የእኔ ፡ የእኔ
መመኪያዬ ፡ ሁሌ ፡ ክብሬ
አንተ ፡ አይደለህ ፡ በዘመኔ
የምጠራው ፡ ዘር ፡ ማንዘሬ
ነፍሴ ፡ ምን ፡ አጣች ፡ አንተን ፡ አግኝታ
ሆንክላት ፡ በጐ ፡ ሆንክላት ፡ ጋሻ
ስለዚህ ፡ በእዚህ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ እንደዚህ ፡
ያምርብሻል ፡ ውዳሴ ፡ ምሥጋና ፡ ነፍሴ ፡ ስታፈልቂ
ምንም ፡ የሌላትን ፡ ምንኛ ፡ ረዳሃት
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እዚህ ፡ አደረስካት
በአመራርህ ፡ ጌታ ፡ እጅግ ፡ እረክታለች
አምላኬ ፡ መሪዬ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ትላለች
ነፍሴ ፡ በአንተ ፡ ሐሴት ፡ ታደርጋለች X፬
እግዚአብሔር ፡ የእኔ ፡ የእኔ ፡ ነው ፡ እያለች X፬
እግዚአብሔር ፡ ክብሬ ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ እያለች X፬
|