ይቅርታ (Yeqerta) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

Awtaru Kebede 5.jpeg


(5)

ይቅርታ
(Yeqerta)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2010)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

አትተወኝ ፡ እባክህ ፡ አትራቀኝ
መንፈስህን ፡ ከውስጤ ፡ አትውሰደው (፪x)

ደግሞ ፡ እንደሚያውቅ
እንደሚያውቅ ፡ ልብ ፡ እንዳለው
ብዙ ፡ ደከምኩኝ ፡ እራሴን ፡ ታዝቤያለሁ (፪x)

አዝ፦ ይቅርታ ፡ ይቅርታ
የእኔ ፡ አባት ፡ ይቅርታ
ይቅር ፡ በለኝና ፡ አስገባኝ
ዳግም ፡ ወደ ፡ ጉያህ (፪x)

ያኔ ፡ ያኔ ፡ አንተን ፡ ያወኩበት ፡ የልጅነት ፡ ኩራት
አይደክመኝም ፡ ፊትህን ፡ ስፈልግ ፡ ጠዋት ፡ ሆነ ፡ ማታ
ምነው ፡ አሁን ፡ ልቤን ፡ ምን ፡ አገኘው ፡ ምን ፡ ገባብኝ
ቆም ፡ ብዬ ፡ ራሴን ፡ ልጠይቀው ፡ ምህረት ፡ አርግልኝ

ወደ ፡ አይምሮዬ ፡ ልመለስና
ማረኝ ፡ ልበለው ፡ በርከክ ፡ ልበልና (፪x)

አዝ፦ ይቅርታ ፡ ይቅርታ
የእኔ ፡ አባት ፡ ይቅርታ
ይቅር ፡ በለኝና ፡ አስገባኝ
ዳግም ፡ ወደ ፡ ጉያህ (፪x)