From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እስከዛሬ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ኖሬ ፡ ተጉዤያለሁ ፡ ብዙ ፡ አብሬ
አንዱ ፡ ሲሄድ ፡ አንዱ ፡ ሲመጣ ፡ አትለወጥ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ
ጥቁር ፡ አይል ፡ ፊትህ ፡ አይቀየር ፡ አትዘጋም ፡ የምህረትን ፡ በር
ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ጭንቁን ፡ እረስቶ ፡ እፎይ ፡ ብሏል ፡ አንተ ፡ ላይ ፡ ታምኖ (፪x)
ያው ፡ ነህ (፰x)
አልወደቅኩም ፡ በፈራሁት ፡ ላይ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ዓይን ፡ ዓይኖቼን ፡ ሲያይ
ከእናት ፡ ከአባት ፡ ከወዳጅ ፡ ይልቅ ፡ ጠብቆኛል ፡ ክፉ ፡ ላይ ፡ እንዳልወድቅ
ዞር ፡ አረገው ፡ ከፊቴ ፡ ቀድሞ ፡ ያንን ፡ ሃዘን ፡ ለእኔ ፡ አስቦ
የተማሰው ፡ ጉድጓድ ፡ ተዘጋ ፡ በአንድ ፡ አፍታ ፡ ለሊቱ ፡ ነጋ (፪x)
ያው ፡ ነህ (፰x)
ብርድ ፡ አለ ፡ የሃሩሩ ፡ ጊዜ
እንደ ፡ ህልም ፡ አለፈ ፡ የሃዘን ፡ ትካዜ (፪x)
ትንግርት ፡ ነው ፡ የፍቅር ፡ ጉልበት ፡ ለወደቀው ፡ የደረሰለት
የአለበት ፡ ጓዳ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ ፡ አቁሞታል ፡ ዘይት ፡ ቀብቶ
ሰው ፡ የለኝም ፡ በግራ ፡ በቀኝ ፡ ጉልበት ፡ ጠፋ ፡ አቅም ፡ አጣሁኝ
ብሎ ፡ ለሚል ፡ ፍቅር ፡ አለው ፡ መላ ፡ ታሪክ ፡ ከፍቶ ፡ ያሳያል ፡ ሌላ
የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ ፡ የእኔ (የእኔ)
የእኔ ፡ አባት ፡ ነህ ፡ የእኔ (የእኔ)
የእኔ ፡ እረኛ ፡ ነህ ፡ የእኔ (ኦኦኦ)
የእኔ ፡ ጋሻ ፡ ነህ ፡ የእኔ (፪x)
የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ ፡ የእኔ (የእኔ)
የእኔ ፡ አባት ፡ ነህ ፡ የእኔ (የእኔ)
የእኔ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ የእኔ (ኦኦኦ)
የእኔ ፡ እረኛ ፡ ነህ ፡ የእኔ (፪x)
|